Gera Qegn Alelem
ኤደን እምሩ · Singles
አዝ፦ ግራ ፡ ቀኝም ፡ አልልም ወደ ፡ ኋላ ፡ ወደ ፡ ፊት በአንተ ፡ ልቤ ፡ እርፍ ፡ ብሏል ሰላም ፡ በአንተ ፡ አግኝቷል በጥያቄዬ ፡ ሁሉ ፡ ጌታ ፡ ጣልቃ ፡ እየገባ ነገሬን ፡ አሳምሮ ፡ ዓይኔ ፡ በደስታ ፡ አነባ ትላንትናም ፡ ዛሬም ፡ አንተው ፡ ነህ ፡ ያለኸኝ አምናን ፡ አሳልፈህ ፡ በዚህ ፡ ያደረስከኝ ለነገም ፡ አልፈራም ፡ አንተ ፡ እያለህልኝ ግራ ፡ ቀኝም ፡ ሳልል ፡ ፀንቼ ፡ ቆምኩኝ ሰላም ፡ ሆንከኝ (፫x) ጌታዬ ፡ ሰላም ፡ ሆንከኝ እረፍት ፡ ሆንከኝ (፫x) አባቴ ፡ እረፍት ፡ ሆንከኝ ዓይኔን ፡ ከሰው ፡ አንስቼ ፡ አንተን ፡ ልመልከት ብትዘገይም ፡ እንኳን ፡ መምጣትህ ፡ አይቀር በመንገድህ/በመቅደስህ ፡ ቆሜ ፡ ጠብቃለሁ በእርግጥም ፡ ስትመጣ ፡ በዓይኔ ፡ አያለሁ (፪x) ለምኜ ፡ አንድም ፡ ቀን ፡ አላፈርኩም ጥያቄም ፡ ሞልቶ ፡ እርፍ ፡ አልኩ ልቤ ፡ በአንተ ፡ ዛሬ ፡ ተደላድሏል አንተን ፡ አንተን ፡ አንተን ፡ አንተን ፡ ይላል (፪x) አዝ፦ ግራ ፡ ቀኝም ፡ አልልም ወደ ፡ ኋላ ፡ ወደ ፡ ፊት በአንተ ፡ ልቤ ፡ እርፍ ፡ ብሏል ሰላም ፡ በአንተ ፡ አግኝቷል በጥያቄዬ ፡ ሁሉ ፡ ጌታ ፡ ጣልቃ ፡ እየገባ ነገሬን ፡ አሳምሮ ፡ ዓይኔ ፡ በደስታ ፡ አነባ ሰላም ፡ ሆንከኝ (፫x) ጌታዬ ፡ ሰላም ፡ ሆንከኝ እረፍት ፡ ሆንከኝ (፫x) አባቴ ፡ እረፍት ፡ ሆንከኝ ትላንትናም ፡ ዛሬም ፡ አንተው ፡ ነህ ፡ ያለኸኝ አምናን ፡ አሳልፈህ ፡ በዚህ ፡ ያደረስከኝ ለነገም ፡ አልፈራም ፡ አንተ ፡ እያለህልኝ ግራ ፡ ቀኝም ፡ ሳልል ፡ ፀንቼ ፡ ቆምኩኝ ምድረ ፡ በዳዬን ፡ ታለመልማለህ ባዶ ፡ ሸለቆዬን ፡ በውኃ ፡ ትሞላለህ በእርግጥም ፡ ኢየሱስ ፡ አንተ ፡ ታማኝ ፡ ነህ (፪x) ወዳጅ ፡ ከአንተ ፡ ሌላ ፡ ለእኔ ፡ ማን ፡ አለ ሚስጥር ፡ ተካፋይ ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ ሁሉን ፡ ነገር ፡ አውቀህ ፡ ትመዝናለህ በእውነትም ፡ ጌታዬ ፡ አንተ ፡ ታማኝ ፡ ነህ ወዳጅ ፡ ከአንተ ፡ ሌላ ፡ ለእኔ ፡ ማን ፡ አለ ሚስጥር ፡ ተካፋይ ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ ሁሉን ፡ ነገር ፡ አውቀህ ፡ ትመዝናለህ በእርግጥም ፡ ኢየሱስ ፡ አንተ ፡ ታማኝ ፡ ነህ ለምኜ ፡ አንድም ፡ ቀን ፡ አላፈርኩም ጥያቄም ፡ ሞልቶ ፡ እርፍ ፡ አልኩ ልቤ ፡ በአንተ ፡ ዛሬ ፡ ተደላድሏል አንተን ፡ አንተን ፡ አንተን ፡ አንተን ፡ ይላል ምድረ ፡ በዳዬን ፡ ታለመልማለህ ባዶ ፡ ሸለቆዬን ፡ በውኃ ፡ ትሞላለህ በእርግጥም ፡ ኢየሱስ ፡ አንተ ፡ ታማኝ ፡ ነህ

