ዞር ብዬ ሳየው
Zor Beyie Sayew
ደረጀ ከበደ · አዳኜ ኢየሱስ · 2010
አጭር ጊዜ አይደለም ለረጅም ዘመናት በድካም በትግል ላያሌ ዓመታት በመውደቅ መነሳት በውጊያ በጭንቀት እንደማያልፍ የለም አለፈ ያ እሳት (፫x) አዝ ዞር ብዬ ሳየው ያሳለፍኩትን አባጣ ጐርባጣ ጉድጓድ ገደሉን ማመን ይሳነኛል ኃይል አገኘው ለካስ ኤልሻዳዩ ጠብቆኝ ቆሜያለሁ ሥሙን አከብራለሁ (፫) መራራ አይታኘክ የመከራ እንጀራ የብቸኝነት ቤት እኔው ከእኔ ጋራ እንቅልፌን አጥቼ ብዙ ለሊት አልፏል ዛሬ ግን ታሪክ ነው ተረት ነው ይወራል (፫x) አዝ ዞር ብዬ ሳየው ያሳለፍኩትን አባጣ ጐርባጣ ጉድጓድ ገደሉን ማመን ይሳነኛል ኃይል ከየት አገኘው ለካስ ኤልሻዳዩ ጠብቆኝ ቆሜያለሁ ሥሙን አከብራለሁ (፫) የሕይወቴ ማብቂያ ዛሬ ነው ያልኩበት ዓይኖቼን ጨፍኜ ሞትን ያሰብኩበት ቀውጤው ሰዓት አልፎ ማየቴ ደንቆኛል ለካስ ጌታ ወዶኝ እጅ እግሬን ጠብቋል (፫x) አዝ ዞር ብዬ ሳየው ያሳለፍኩትን አባጣ ጐርባጣ ጉድጓድ ገደሉን ማመን ይሳነኛል ኃይል ከየት አገኘው ለካ ኤልሻዳዩ ጠብቆኝ ቆሜያለሁ ሥሙን አከብራለሁ (፫x) የአብርሃም አምላክ በክንፉ ሸሸገኝ ለካስ መጐዳቴን ተጐሳቁዬ አየኝ ያን ሁሉ ሻካራ ያን ሁሉ ጐርባጣ ጌታ ብርታት ሆነኝ ችዬው እንድወጣ (፫x) አዝ ዞር ብዬ ሳየው ያሳለፍኩትን አባጣ ጐርባጣ ጉድጓድ ገደሉን ማመን ይሳነኛል ኃይል ከየት አገኘው ለካስ ኤልሻዳዩ ጠብቆኝ ቆሜያለሁ ሥሙን አከብራለሁ (፫)

