የነፍሴ ንጉሥ
Yenefsie Negus
ደረጀ ከበደ · ስብስብ
አዝ፦ የነፍሴ ፡ ንጉሥ ፡ ኢየሱስ የሕይወቴ ፡ ንጉሥ ፡ ኢየሱስ በሰማይ ፡ በምድር ፡ ቅዱስ ፡ ቅዱስ የነፍሴ ፡ ንጉሥ (፪x) በድንግዝግዝ ፡ ብርሃን ፡ በምኞት ፡ ሸለቆ ቆሜ ፡ ሳነባ ፡ አየኝ ፡ ሕይወቴ ፡ ተነክቶ የዘረጋው ፡ እጁ ፡ አልደርስለት ፡ ብሎ አወጣኝ ፡ አምላኬ ፡ ለእኔ ፡ ተንጠልጥሎ አዝ፦ የነፍሴ ፡ ንጉሥ ፡ ኢየሱስ የሕይወቴ ፡ ንጉሥ ፡ ኢየሱስ በሰማይ ፡ በምድር ፡ ቅዱስ ፡ ቅዱስ የነፍሴ ፡ ንጉሥ (፪x) እጆቹ ፡ ቆሰሉ ፡ ግንባሩ ፡ ተበሳ ለእኔ ፡ ለሙት ፡ ሕይወት ፡ እንዲኖረኝ ፡ ተስፋ ጐኑን ፡ ለጦር ፡ ሰጥቶ ፡ ደሙን ፡ አጐረፈ የእኔን ፡ አፈር ፡ ገላ ፡ ከሞት ፡ አተረፈ አዝ፦ የነፍሴ ፡ ንጉሥ ፡ ኢየሱስ የሕይወቴ ፡ ንጉሥ ፡ ኢየሱስ በሰማይ ፡ በምድር ፡ ቅዱስ ፡ ቅዱስ የነፍሴ ፡ ንጉሥ (፪x) ጀርባውን ፡ ለጅራፍ ፡ አጋልጦ ፡ ሰጠና ተዘነጋ ፡ በእርሱ ፡ የእኔ ፡ ጉስቁልና እርቃኑን ፡ ተጋልጦ ፡ ሆኖ ፡ ጐስቋላ ፡ ሰው ሚስጢሬን ፡ ደብቋል ፡ ሕይወቴ ፡ እንዴት ፡ ትርሳው? አዝ፦ የነፍሴ ፡ ንጉሥ ፡ ኢየሱስ የሕይወቴ ፡ ንጉሥ ፡ ኢየሱስ በሰማይ ፡ በምድር ፡ ቅዱስ ፡ ቅዱስ የነፍሴ ፡ ንጉሥ (፪x) የድካሙ ፡ ብዛት ፡ ለእኔ ፡ ፋታ ፡ ሆነኝ የቀራንዮ ፡ ደም ፡ ከኃጢአት ፡ አዳነኝ ጽድቁን ፡ ተመርኩዤ ፡ ስራዬን ፡ ደብቄ ተጓዝኩኝ ፡ ከእርሱ ፡ ጋር ፡ ድካሜን ፡ አውቄ አዝ፦ የነፍሴ ፡ ንጉሥ ፡ ኢየሱስ የሕይወቴ ፡ ንጉሥ ፡ ኢየሱስ በሰማይ ፡ በምድር ፡ ቅዱስ ፡ ቅዱስ የነፍሴ ፡ ንጉሥ (፪x)

