Gubae

የሚመጣ

Yemimeta

ደረጀ ከበደ · አዳኜ ኢየሱስ · 2010

የሚመጣ ፡ የሚከብር ፡ የሚነግስ ፡ ኢየሱስ ተቀናቃኝ ፡ የለው ፡ ወይም ፡ ባላጋራ ፊት ፡ ለፊት ፡ የሚቆም ፡ ግጥሚያ ፡ ከርሱ ፡ ጋራ (፪x) በአህዛብ ፡ ፊት ፡ ሊከብር ፡ በድንቅ ፡ ይገለጣል ብንወድም ፡ ባንወድም ፡ ኢየሱስ ፡ ይነግሳል (፪x) የሚመጣ ፡ የሚከብር ፡ የሚነግስ ፡ ኢየሱስ (፪x) ከእንግዲህ ፡ ለውርደት ፡ ለሞት ፡ አይሰጥም አንድ ፡ ጊዜ ፡ በመስቀል ፡ ፈጽሟል ፡ ሁሉንም (፪x) ያነ ፡ እዳ ፡ ሊከፍል ፡ ዛሬ ፡ ዳኛ ፡ ሆኖ ይመጣል ፡ ጌታችን ፡ በክብር ፡ ተክኖ (፪x) የሚመጣ ፡ የሚከብር ፡ የሚነግስ ፡ ኢየሱስ (፪x) ከዘመናት ፡ በፊት ፡ ሁሉን ፡ ጥለው ፡ ያሉ ለርሱ ፡ የተገዙ ፡ ሞፈር ፡ ቀንበር ፡ ሳይሉ (፪x) በታላቅ ፡ እልልታ ፡ በሆታ ፡ በደስታ በአይናቸው ፡ ያዩታል ፡ የዘላለሙን ፡ ጌታ (፪x) የሚመጣ ፡ የሚከብር ፡ የሚነግስ ፡ ኢየሱስ (፪x) ከደመናው ፡ መሃል ፡ ግርማው ፡ የሚያስፈራ በመላዕክት ፡ ታጅቦ ፡ ከአገልጋዮች ፡ ጋራ (፪x) የቅዱሳን ፡ አባት ፡ ስሙም ፡ አማኑኤል በከዋክብት ፡ ደምቆ ፡ አሜን ፡ ከተፍ ፡ ይላል (፪x) የሚመጣ ፡ የሚከብር ፡ የሚነግስ ፡ ኢየሱስ (፪x)

ደረጀ ከበደ · ሁሉም ዘማሪዎች