Gubae

ያምላኬ ቃል አያረጅም

Yamlakie Qal Ayarejem

ደረጀ ከበደ · ስብስብ

አዝ፦ ያምላኬ ፡ ቃል ፡ አያረጅም የኢየሱስ ፡ ቃል ፡ አያረጅም ዘለዓለም ፡ ይኖራል ፡ እያበራ ከሚያምኑት ፡ ጋራ (፪x) ተስፋ ፡ ስቆርጥ ፡ ያጽናናኛል አቅፎ ፡ ደግፎ ፡ ያኖረኛል በደሙ ፡ አጥቦ ፡ አንጽቶኛል ኮብልዬ ፡ እንዳልሄድ ፡ ይጠብቀናል አዝ፦ ያምላኬ ፡ ቃል ፡ አያረጅም የኢየሱስ ፡ ቃል ፡ አያረጅም ዘለዓለም ፡ ይኖራል ፡ እያበራ ከሚያምኑት ፡ ጋራ (፪x) በዓለም ፡ ጉዞዬ ፡ ይደግፈኛል ፍፁም ፡ ላይተወኝ ፡ ተስፋ ፡ ሰጥቶኛል አልተወውም ፡ አይተወኝም የኢየሱሴ ፡ ነኝ ፡ እስከዘለዓለም አዝ፦ ያምላኬ ፡ ቃል ፡ አያረጅም የኢየሱስ ፡ ቃል ፡ አያረጅም ዘለዓለም ፡ ይኖራል ፡ እያበራ ከሚያምኑት ፡ ጋራ (፪x) ሥጋዬ ፡ ደክሞ ፡ ነፍሴ ፡ ተጨንቃ ፡ ስታንቀላፋ የአምላኬ ፡ ቃል ፡ ያነቃኛል ፡ በሰጠኝ ፡ ተስፋ ልጁ ፡ ሆኛለሁ ፡ ዳግም ፡ ወልዶኛል ኃጢአቴን ፡ ሁሉ ፡ ደምስሶልኛል ጌታዬ ፡ አቅፎኝ ፡ በእርሱ ፡ ስር ፡ ካለሁ ብርሃን ፡ እያየሁ ፡ እጓዛለሁ አዝ፦ ያምላኬ ፡ ቃል ፡ አያረጅም የኢየሱስ ፡ ቃል ፡ አያረጅም ዘለዓለም ፡ ይኖራል ፡ እያበራ ከሚያምኑት ፡ ጋራ (፪x) ከሚያምኑት ፡ ጋራ

ደረጀ ከበደ · ሁሉም ዘማሪዎች