Gubae

ነፍሴን ለሞት ሽጬ

Nefsien Lemot Shechie

ደረጀ ከበደ · ስብስብ

የዓለም ፡ መራቀቅ ፡ እኔን ፡ አይገደኝም የጠላት ፡ ድንፋታም ፡ አያስጨንቀኝም አምላኬን ፡ አውቃለሁ ፡ ፍፁም ፡ የለም ፡ ቢሉ እኔስ ፡ አለ ፡ እላለሁ ፡ ተናግሮኛል ፡ ቃሉ አዝ፦ ነፍሴን ፡ ለሞት ፡ ሽጬ ፡ አለሁኝ ፡ አልልም ላያዛልቅ ፡ ኑሮ ፡ አምላኬን ፡ አልክድም እኔ ፡ እኔነቴን ፡ እስካላዘዝኩበት የሚያዝበት ፡ አለ ፡ ሌላ ፡ ባለንብረት ይህን ፡ ክቡር ፡ ገላ ፡ በዋዛ ፡ አላየውም የፈጠረኝንም ፡ አምላኬን ፡ አልክድም አዝ፦ ነፍሴን ፡ ለሞት ፡ ሽጬ ፡ አለሁኝ ፡ አልልም ላያዛልቅ ፡ ኑሮ ፡ አምላኬን ፡ አልክድም ገንዘብ ፡ ነው ፡ ጌጣጌጥ ፡ የትኛው ፡ ነው ፡ ትርፉ ከአምላክ ፡ ተነጥሎ ፡ በዓለም ፡ ውስጥ ፡ መክነፉ ሁሉም ፡ ሥጋ ፡ ለባሽ ፡ ወደ ፡ አፈር ፡ ከሄደ ዋጋው ፡ የላቀ ፡ ነው ፡ አምላክን ፡ ያልካደ አዝ፦ ነፍሴን ፡ ለሞት ፡ ሽጬ ፡ አለሁኝ ፡ አልልም ላያዛልቅ ፡ ኑሮ ፡ አምላኬን ፡ አልክድም

ደረጀ ከበደ · ሁሉም ዘማሪዎች