Gubae

መከራ ሳይመጣ

Mekera Saymeta

ደረጀ ከበደ · ዝም አልልም

ሕይወት በሰላሙ ምንኛ ይጥማል እግዚአብሔር ቅርብ ነው ጸሎትም ይሰማል የፈለጉት ሲሆን ደጅ ቤት ሲሞላ ክርስትና ግሩም ግሩም እንደ ሌላ አዝ፡- መከራ ሳይመጣ ሁሉም ክርስቲያን ነው ሁል ጊዜ ሀሌሉያ ከአፉ ማይለየው መበጠር ሲከሰት ሁሉም ይሸበራል ጠመንጃው ጥይቱ ከእጁ ይሽቀነጠራል ገለባው ከስንዴው መለየት ሲጀምር አስመሳይ ሲሯሯጥ ይታያል ግርግር ሀሳዊው ሰባኪ ከመድረክ ይሮጣል ዘማሪው ደብተሩን ጉያው ይደብቃል አዝ፡- መከራ ሳይመጣ ሁሉም ክርስቲያን ነው ሁል ጊዜ ሀሌሉያ ከአፉ ማይለየው መበጠር ሲከሰት ሁሉም ይሸበራል ጠመንጃው ጥይቱ ከእጁ ይሽቀነጠራል ያ ግን ያምላክ ወዳጅ ኢየሱስን ያውቃል አታላይ ሲገለጥ ቀስቱን ይደግናል እሳቱን ባህሩን ታግሶ ተሸግሮ ጌታን ይገናኛል ክብር ተሸልሞ አዝ፡- መከራ ሳይመጣ ሁሉም ክርስቲያን ነው ሁል ጊዜ ሀሌሉያ ከአፉ ማይለየው መበጠር ሲከሰት ሁሉም ይሸበራል ጠመንጃው ጥይቱ ከእጁ ይሽቀነጠራል

ደረጀ ከበደ · ሁሉም ዘማሪዎች