ብልህ ሰው ነፍሱን ያድናል
Beleh Sew Nefsun Yadenal
ደረጀ ከበደ · መንግሥተ ሰማይ · 1980
አዝ፦ ጌታ ሆይ ከሞት ሕይወት ይመረጣል ብልህ ሰው ነፍሱን ያድናል በስምህ ፡ ትዕዛዝ ፡ ስር ፡ ያድራል በልቡ ፡ አንተን ፡ ፈላጊ ስምህን ፡ ጠሪ ፡ ይባረካል በኑሮ ፡ የሚያስቀድምህ የደስታን ፡ ካባን ፡ ይደርባል ከእርኩሰት ፡ ታርቀዋለህ በልቡ ፡ ዙፋን ፡ ላይ ፡ ነግሰህ ሰላምን ፡ በውስጡ ፡ አኑሮ ይጓዛል ፡ ደስታን ፡ ጨምሮ አዝ፦ ጌታ ፡ ሆይ ከሞት ሕይወት ይመረጣል ብልህ ሰው ነፍሱን ያድናል በስምህ ፡ ትዕዛዝ ፡ ስር ፡ ያድራል ከኋለኛው ፡ ሃዘን ፡ ይልቅ የአሁኑን ፡ ጉስቁልና ፡ መርጦ ጊዜያዊውን ፡ ተድላ ፡ ንቆ ነፍሱን ፡ ከሥጋው ፡ ያየ ፡ አብልጦ ብልህ ፡ ነው ፡ ጠቢብ ፡ አዋቂ የሰማይ ፡ ሃገር ፡ ዘላቂ ዘለዓለም ፡ እረፍትን ፡ አይቷል ለተስፋው ፡ ምድር ፡ ተመርጧል አዝ፦ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ከሞት ሕይወት ይመረጣል ብልህ ሰው ነፍሱን ያድናል በስምህ ታዛ ስር ያድራል በለመለመ ፡ መስክ ፡ አድሮ የጠራ ፡ ምንጭ ፡ ውኃ ፡ ጠጥቶ በአምላኩ ፡ እንክብካቤ ፡ አድርጐ መጓዙን ፡ የሰው ፡ ልጅ ፡ አጥላልቶ ከስታለች ፡ ተርባ ፡ ነፍሱ ታውኳል ፡ ሥጋ ፡ መንፈሱ ይመለስ ፡ ሚወድ ፡ ይመለስ ሳይወድቅ ፡ ጉልበቱ ፡ ሳይፈር አዝ፦ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ከሞት ፡ ሕይወት ፡ ይመረጣል ብልህ ሰው ነፍሱን ያድናል በስምህ ታዛ ስር ያድራል (፬x)

