Gubae

አልተማረም አሉኝ

Altemarem Alugn

ደረጀ ከበደ · ስብስብ

የማመልከው ፡ አምላክ ፡ ሳይንስ ፡ አይጨብጠው የእብድ ፡ ቃላት ፡ ብዛት ፡ በእውነት ፡ አይገምተው መስፈሳዊ ፡ አይኖች ፡ ተከፍተው ፡ ካላዩት ቃሉ፡ ሞኝነት ፡ ነው ፡ አውቀናል ፡ ለሚሉት አዝ፦ ሞኝ ፡ ነው ፡ አልተማረም ፡ አሉኝ ለእግዚአብሔር ፡ አድሬለት ፡ ቢያዩኝ ትርፌን ፡ እና ፡ ጥቅሜን ፡ ባለማወቃቸው እኔ ፡ አዘንኩላቸው (፪x) ይልቅስ ፡ ሳይጨልም ፡ መዝጊያው ፡ ሳይቆለፍ የሰው ፡ ልጅ ፡ ይመለስ ለሚጠፋው ፡ አለም ፡ ጉልበቱን ፡ ከማፍሰስ (፪x) የሚጠፋ ፡ ጥሪት ፡ ማከማቸት ፡ ትቼ ዘላለማዊውን ፡ ለማግኘት ፡ ዘይጄ ጌታዬን ፡ የሙጥኝ ፡ ብዬ ፡ መወሰኔ ከአዋቂዎች ፡ በላይ ፡ አልሆንኩም ፡ ወይ ፡ እኔ አዝ፦ ሞኝ ፡ ነው ፡ አልተማረም ፡ አሉኝ ለእግዚአብሔር ፡ አድሬለት ፡ ቢያዩኝ ትርፌን ፡ እና ፡ ጥቅሜን ፡ ባለማወቃቸው እኔ ፡ አዘንኩላቸው (፪x) ይልቅስ ፡ ሳይጨልም ፡ መዝጊያው ፡ ሳይቆለፍ የሰው ፡ ልጅ ፡ ይመለስ ለሚጠፋው ፡ አለም ፡ ጉልበቱን ፡ ከማፍሰስ (፪x) ምድር ፡ እና ፡ ሰማይን ፡ ያበጀው ፡ ፈጣሪ አይመረመርም ፡ ገብቶ ፡ ልብራቶሪ ቁጥርን ፡ ከቁጥር ፡ ጋር ፡ ሲያጋጩ ፡ ቢኖሩ አያዩትም ፡ ጌታን ፡ እሩቅ ፡ ነው ፡ ሃገሩ አዝ፦ ሞኝ ፡ ነው ፡ አልተማረም ፡ አሉኝ ለእግዚአብሔር ፡ አድሬለት ፡ ቢያዩኝ ትርፌን ፡ እና ፡ ጥቅሜን ፡ ባለማወቃቸው እኔ ፡ አዘንኩላቸው (፪x) ይልቅስ ፡ ሳይጨልም ፡ መዝጊያው ፡ ሳይቆለፍ የሰው ፡ ልጅ ፡ ይመለስ ለሚጠፋው ፡ አለም ፡ ጉልበቱን ፡ ከማፍሰስ (፪x) ሰአቱ ፡ ገና ፡ አለ ፡ ጊዜአችን ፡ አልከፋም እግዚአብሔር ፡ ደጁን ፡ በሰው ፡ ልጅ ፡ አልዘጋም ከማንቀላፋቱ ፡ ነቅቶ ፡ ለታረመ ብርሃን ፡ ነው ፡ ገና ፡ ዛሬ ፡ መች ፡ ጨለመ አዝ፦ ሞኝ ፡ ነው ፡ አልተማረም ፡ አሉኝ ለእግዚአብሔር ፡ አድሬለት ፡ ቢያዩኝ ትርፌን ፡ እና ፡ ጥቅሜን ፡ ባለማወቃቸው እኔ ፡ አዘንኩላቸው (፪x) ይልቅስ ፡ ሳይጨልም ፡ መዝጊያው ፡ ሳይቆለፍ የሰው ፡ ልጅ ፡ ይመለስ ለሚጠፋው ፡ አለም ፡ ጉልበቱን ፡ ከማፍሰስ (፪x)

ደረጀ ከበደ · ሁሉም ዘማሪዎች