አዳኜ ኢየሱስ
Adagnie Yesus
ደረጀ ከበደ · አዳኜ ኢየሱስ · 2010
አዳኜ ኢየሱስ ገናናው የእጄን ሰንሰለት በጠሰው ተመስገን ልበል ልቀኝለት በእግሩ ሥር ልውደቅ ልስገድለት ይህም አነሰበት ነፍሴን አስጨንቋት የጠላቴ ጩኸት አይኖቼን ባቀና ከላይ ስመለከት ከመቅደሱ ሆኖ እምባዬን አበሰ ያሰረኝን ገመድ ጌታ በጣጠሰ አዳኜ ኢየሱስ ገናናው የእጄን ሰንሰለት በጠሰው ተመስገን ልበል ልቀኝለት በእግሩ ሥር ልውደቅ ልስገድለት ይህም አነሰበት የሞት ቀንበር ከቦኝ ያመፅ ፈሳሽ ውጦኝ ሲኦል አፉን ከፍቶ ባጥንቴ አስቀርቶኝ ስሞታ ነገርኩኝ ላምላኬ ሳልሰለች እግዚአብሔር ተቆጣ ምድር ተናወጠች አዳኜ ኢየሱስ ገናናው የእጄን ሰንሰለት በጠሰው ተመስገን ልበል ልቀኝለት በእግሩ ሥር ልውደቅ ልስገድለት ይህም አነሰበት ጠላቴን ሰበረ እንዳያንሰራራ ከቁጣው ጢስ ወጣ ፍምም ከሱ በራ ባእድ የረገጠኝ እንደመንገድ ጭቃ ነፃነቴን ሰጠኝ መቆዘሜ አበቃ አዳኜ ኢየሱስ ገናናው የእጄን ሰንሰለት በጠሰው ተመስገን ልበል ልቀኝለት በእግሩ ሥር ልውደቅ ልስገድለት ይህም አነሰበት ዛሬማ ሰው ሆኜ ቀስት እገትራለሁ በኮረብታ ቆሜ ምሥጋና እሰዋለሁ ፅኑ እግር ለሰጠኝ የማይንሸራተት ለናዝሬቱ ኢየሱስ እጥፍ ልስገድለት አዳኜ ኢየሱስ ገናናው የእጄን ሰንሰለት በጠሰው ተመስገን ልበል ልቀኝለት በእግሩ ሥር ልውደቅ ልስገድለት ይህም አነሰበት

