Gubae

የፀና ግንብ

Yetsena Ginb

ዳዊት ወልዴ · መዝሙር ፺ ፩ · 2005

የጸና ፡ ግንብ ፡ ነው ፡ ያንተ ፡ ሥም ፡ ጌታዬ በመከራዬ ፡ ቀን ፡ ሆነኝ ፡ መጠጊያዬ ጻድቅ ፡ ሥምህን ፡ ጠርቶ ፡ ከጉዳት ፡ ያመልጣል ካስፈሪው ፡ ጨለማ ፡ ከጉድጓድ ፡ ይወጣል አዝ:- ሥምህ ፡ ይክበር ፡ አባቴ ፡ ሥምህ ፡ ይክበር ፡ መድኃኒቴ ሥምህ ፡ ይክበር ፡ አባቴ ፡ ሥምህ ፡ ይክበር ፡ መድኃኒቴ ፡ መድኃኒቴ (፪x) ሥምህ ፡ ከሥም ፡ ሁሉ ፡ በላይ ፡ ነው ፡ አምላኬ ፈጥነህ ፡ ትደርሳለህ ፡ ስጮህ ፡ ተንበርክኬ ከጨካኙ ፡ አውሬ ፡ ከሞት ፡ ኃይል ፡ ያድናል የሥምህ ፡ ጉልበቱ ፡ ጠላቴን ፡ ይጥላል አዝ:- ሥምህ ፡ ይክበር ፡ አባቴ ፡ ሥምህ ፡ ይክበር ፡ መድኃኒቴ ሥምህ ፡ ይክበር ፡ አባቴ ፡ ሥምህ ፡ ይክበር ፡ መድኃኒቴ ፡ መድኃኒቴ (፪x) ብዙዎች ፡ ተነሱ ፡ በኃይል ፡ የገነኑ ዝናቸው ፡ የናኘ ፡ ላፍታ ፡ ለሰሞኑ ዝንታለም ፡ አልቆዩም ፡ እንደጥላ ፡ አልፈዋል የኔ ፡ ጌታዬ ፡ ሥም ፡ ዛሬም ፡ ድንቅ ፡ ይሰራል አዝ:- ሥምህ ፡ ይክበር ፡ አባቴ ፡ ሥምህ ፡ ይክበር ፡ መድኃኒቴ ሥምህ ፡ ይክበር ፡ አባቴ ፡ ሥምህ ፡ ይክበር ፡ መድኃኒቴ ወደ ፡ ኃይሉ ፡ ችሎት ፡ ገባሁ ፡ ያለከልካይ አጋፋሪ ፡ አልቆመ ፡ ዘበኛ ፡ ደጁ ፡ ላይ በጨነቀኝ ፡ ጊዜ ፡ በየትኛውም ፡ ቦታ ፊቱ ፡ አፈሳለሁ ፡ የእንባዬን ፡ ጠብታ የልቤን ፡ ብሶት ፡ ያያል ፡ ጩኸቴንም ፡ ያዳምጣል እንባዬን ፡ ያብስልኛል ፡ እንደንስር ፡ ያድሰኛል የጸና ፡ ግንብ ፡ ነው ፡ ያንተ ፡ ስም ፡ ጌታዬ በመከራዬ ፡ ቀን ፡ ሆነኝ ፡ መጠጊያዬ ጻድቅ ፡ ስምህን ፡ ጠርቶ ፡ ከጉዳት ፡ ያመልጣል ካስፈሪው ፡ ጨለማ ፡ ከጉድጓድ ፡ ይወጣል አዝ:- ሥምህ ፡ ይክበር ፡ አባቴ ፡ ሥምህ ፡ ይክበር ፡ መድኃኒቴ ሥምህ ፡ ይክበር ፡ አባቴ ፡ ሥምህ ፡ ይክበር ፡ መድኃኒቴ ፡ መድኃኒቴ (፪x) ሥምህን ፡ ሳነሳሳ ፡ ሰይጣን ፡ ይሸበራል ባንድ ፡ መንገድ ፡ መጥቶ ፡ በብዙ ፡ ይሸሻል በተኩላና ፡ በእባቡ ፡ ላይ ፡ እጫማለሁ አንበሳ ፡ ዘንዶውን ፡ እረጋግጣለሁ በጌታ ፡ እታመናለሁ ፡ ሥሙንም ፡ አውቀዋለሁ ስጠራው ፡ ይመልስልኛል ፡ ማዳኑንም ፡ ያሳየኛል ፡ ያከብረኛል (፪x)

ዳዊት ወልዴ · ሁሉም ዘማሪዎች