ይህ ለእኔ ክብር ነው
Yeh Lenie Keber New
ዳዊት ወልዴ · መዝሙር ፺ ፩ · 2005
አዝ፦ የሰማይ ፡ የምድር ፡ የፍጥረት ፡ ንጉሥ ለእኔ ፡ ይህ ፡ ክብር ፡ ነው ፡ አንተን ፡ ማወደስ የቁጣ ፡ ልጅ ፡ ሳለሁ ፡ ቀድሞ ፡ ከፍጥረቴ ሳስብ ፡ ይደንቀኛል ፡ በስምህ ፡ መጠራቴ ተደምስሶ ፡ ኃጢአቴ ፡ የዕዳ ፡ ጽህፈቴ ፡ በአንተ ፡ በመታየቴ ስምህን ፡ አነግሣለሁ ፡ ማዳንህን ፡ ስላየሁ መዝሙር ፡ እዘምራለሁ ፡ ፍቅርህን ፡ ስላየሁ እጥፍ ፡ አሰግዳለሁ ፡ ለክቡርነትህ አምልኮ ፡ አቀርባለሁ ፡ ለአምላክነትህ አዝ፦ የሰማይ ፡ የምድር ፡ የፍጥረት ፡ ንጉሥ ለእኔ ፡ ይሄ ፡ ክብር ፡ ነው አንተን ፡ ማወደስ ፡ አንተን ፡ ማሞገስ ዝናህን ፡ ሰምቼ ፡ በዓይኖቼ ፡ አይቼ ለክብርህ ፡ ሰገድኩኝ ፡ ጌታ ፡ አምላኬ ፡ አልኩህ ቤቱን ፡ የሞሉትን ፡ ፈሪሳውያንን ፡ ሳትፈራ የናርዶስን፡ ሽቶ ፡ በእግሮቹ ፡ ሥር ፡ ሰብራ እንባዋን ፡ አፍስሳ ፡ ክብሯን ፡ ሁሉ ፡ ጥላ እንዳመለከችው ፡ የነፍሷን ፡ ከለላ እኔም ፡ ከሕይወቴ ፡ ሳልቆጥብ ፡ ከአንጀቴ ፡ ዜማ ፡ መስዋዕቴ አዝ፦ የሰማይ ፡ የምድር ፡ የፍጥረት ፡ ንጉሥ ለእኔ ፡ ይሄ ፡ ክብር ፡ ነው አንተን ፡ ማወደስ ፡ አንተን ፡ ማሞገስ ዝናህን ፡ ሰምቼ ፡ በዓይኖቼ ፡ አይቼ ለክብርህ ፡ ሰገድኩኝ ፡ ጌታ ፡ አምላኬ ፡ አልኩህ ገና ፡ በሩቅ ፡ ሳለሁ ፡ በስሜ ፡ ያወቅከኝ የርስትህ ፡ ተካፋይ ፡ ወራሽ ፡ ያደረከኝ ለሰው ፡ አስቸጋሪ ፡ ድካም ፡ ጉድለቴን ፡ ችለህ ስወድቅ ፡ ስነሳ ፡ አይዞህ ፡ ልጄ ፡ ብለህ በክንድህ ፡ ደግፈህ ፡ በፍቅር ፡ እጅህ ፡ ዳሰህ አቆምቀኝ ፡ ሰው ፡ አርገህ ሥምህን ፡ አነግሳለሁ ፡ ማዳንን ፡ ስላየሁ መዝሙር ፡ እዘምራለሁ ፡ ፍቅርህን ፡ ስላየሁ እጥፍ ፡ አሰግዳለሁ ፡ ለክቡርነትህ አምልኮ ፡ አቀርባለሁ ፡ ለአምላክነትህ አዝ፦ የሰማይ ፡ የምድር ፡ የፍጥረት ፡ ንጉሥ ለእኔ ፡ ይሄ ፡ ክብር ፡ ነው አንተን ፡ ማወደስ ፡ አንተን ፡ ማሞገስ ዝናህን ፡ ሰምቼ ፡ በዓይኖቼ ፡ አይቼ ለክብርህ ፡ ሰገድኩኝ ፡ ጌታ ፡ አምላኬ ፡ አልኩህ ጌታ ፡ አምላኬ ፡ አልኩህ (፬x)

