Gubae

ፈገግታ

Smile

ዳዊት ወልዴ · መዝሙር ፺ ፩ · 2005

የትም ፡ ባክኜ ፡ እንዳልጠፋ ፡ እንደሌላቸው ፡ ተስፋ አምላኬ ፡ ጐዳናዬን ፡ መንገዴን ፡ አሰፋ ደረቁን ፡ ምድረ ፡ በዳ ፡ በውሃ ፡ እንዲረካ በምንጩ ፡ ደስ ፡ አሰኘኝ ፡ ጨለማዬ ፡ ፈካ የመርገም ፡ ጨርቄን ፡ ቀደደዉ ፡ መተላለፌን ፡ አራቀዉ እግሬን ፡ አጸና ፡ በከፍታ ፡ ወዶ ፡ አዳነኝ ፡ የኔ ፡ ጌታ በተከበበች ፡ ከተማ ፡ አጽናኝ ፡ ድምጽ ፡ እያሰማ በአስደናቂ ፡ ምሕረቱ ፡ አኖረኝ ፡ በቤቱ ሲጠብቀኝ ፡ መች ፡ ሰንፎ ፡ አቤት ፡ ስንቱን ፡ አሳልፎ ከቶ ፡ አለ ፡ ለታምራቱ ፡ ከልቤ ፡ ተጽፎ በባዕድ ፡ ምድር ፡ ጓደኛዬ ፡ (ጓደኛዬ) ሳዝን ፡ መጽናኛዬ ፡ (መጽናኛዬ) ታሪኬን ፡ ሞላው ፡ በመዝገቡ ከፍ ፡ ይበልልኝ ፡ ታላቅ ፡ ስሙ አፌን ፡ ሞላው ፡ በሳቅ ፡ ዝማሬ ፡ ተረጋጋ ፡ ዙሪያ ፡ ሰፈሬ ስለ ፡ ሥሙ ፡ ያደረገው ፡ ምስጋናው ፡ እጅግ ፡ ብዙ ፡ ነው (፪x) ጌታ ፡ ፊት ፡ አይቶ ፡ አያዳላ ፡ አምላኬ ፡ የምስኪን ፡ ጥላ ተማምነው ፡ ለጠበቁት ፡ ይደርሳል ፡ ሲጠሩት እኔም ፡ እርሱን ፡ ታምኜ ፡ በእድሜ ፡ በሕይወት ፡ ዘመኔ አልቀረሁም ፡ በከንቱ ፡ አለሁኝ ፡ በቤቱ አባ ፡ አባት ፡ ብዬ ፡ ተጣርቼ ፡ (ሥሙን ፡ ጠርቼ) በእምባ ፡ በጸሎት ፡ ደጅ ፡ ጠንቼ ምልጃዬን ፡ ሰምቶ ፡ (ምልጃዬን ፡ ሰምቶ) ፡ አልጨከነም (ምሕረቱን ፡ ከእኔ) ፡ ምሕረቱን ፡ ከእኔ ፡ አላራቀም አፌን ፡ ሞላው ፡ በሳቅ ፡ ዝማሬ ፡ ተረጋጋ ፡ ዙሪያ ፡ ሰፈሬ ስለ ፡ ሥሙ ፡ ያደረገው ፡ ምስጋናው ፡ እጅግ ፡ ብዙ ፡ ነው (፯x) ምስጋናው ፡ እጅግ ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ (፫x)

ዳዊት ወልዴ · ሁሉም ዘማሪዎች