Gubae

ክብር ለኢየሱስ

Kibir LeEyesus

ዳዊት ወልዴ · መዝሙር ፺ ፩ · 2005

ለጻድቁ ፡ ክብር ፡ ክብር ፡ ይሁን የሚል ፡ ዝማሬ ፡ ከምድር ፡ ዳር ፡ ሲሰማ እኔም ፡ ድምፄን ፡ አብሬ ፡ አነሳለሁ ለእግዚአብሔር ፡ ክብር ፡ እዘምራለሁ ቅዱሳን ፡ መላዕክቱ ፡ ባንድነት ሌሊትና ፡ ቀንም ፡ ሚሰግዱለት የምድር ፡ ፍጥረታት ፡ ጉዑዛን ፡ ሁሉ ለቅዱሱ ፡ መንፈስ ፡ ይገዛሉ ደሙን ፡ አፍስሷልና ፡ እኔን ፡ ሊገዛ ለአዳኜ ፡ ኢየሱስ ፡ ምስጋናው ፡ ይብዛ (፪x) ክብር ፡ ለእግዚአብሔር ክብር ፡ ለኢየሱስ ክብር ፡ ለመንፈስ ፡ ቅዱስ ሥሙ ፡ በዓለም ፡ ይንገስ (፲፬x)

ዳዊት ወልዴ · ሁሉም ዘማሪዎች