Gubae

ጌታ እንደተናገረ

Gieta Endetenagere

ዳዊት ወልዴ · መዝሙር ፺ ፩ · 2005

ጌታዬ ፡ አምላኬ ፡ ይዋሽ ፡ ዘንድ ፡ እንደሰው ፡ አይደለምና ላይችል ፡ ላይፈጽም ፡ ላይሞላ ፡ እንዲያው ፡ ቃል ፡ አይገባምና እርሱ ፡ ይሁን ፡ ያለው ፡ ይሆናል ፡ ቃሉ ፡ መች ፡ መሬት ፡ ጠብ ፡ ይላል የፍጥረት ፡ ሁሉ ፡ ገዢ ፡ ነው ፡ እንደወደደ ፡ ያደርጋል የጠራኝ ፡ ጌታዬ ፡ የታመነ ሁሉ ፡ እንደቃሉ ፡ የሆነ ምንተስኖት ፡ የማመልከዉ ለሀይሉ ፡ ወሰን ፡ የሌለዉ አዝ:- ጌታ ፡ እንደተናገረ ፡ እንዲሁ ፡ ስለሚፈጽመው ለነገ ፡ መጨነቄን ፡ ትቼ ፡ ዛሬ ፡ ምስጋናዬን ፡ እሰዋለሁ (፪x) አብርሃምን ፡ ከዑር ፡ ሲያወጣው ፡ ወዶ ፡ ሲመርጠው ፡ ሲጠራው እንዲያው ፡ በከንቱ ፡ አይደለም ፡ ወደ ፡ ከነዓን ፡ የመራው በበረከቱ ፡ ባረከው ፡ በመታዘዙ ፡ አከበረው የተስፋ ፡ ቃሉን ፡ ፈጽሞ ፡ የትውልድ ፡ አባት ፡ አደረገው የጠራኝ ፡ ጌታዬ ፡ የታመነ ሁሉ ፡ እንደቃሉ ፡ የሆነ ምንተስኖት ፡ የማመልከዉ ለሀይሉ ፡ ወሰን ፡ የሌለዉ ሆ ፡ ሆ ፡ ሆ (፰x) ምንተስኖት ፡ ምንተስኖት ምን ፡ አቅቶት ፡ ማን ፡ አግዶት እንደወደደ ፡ ያደርጋል ሰይጣንን ፡ ያንበረክካል (፪x) አዝ:- ጌታ ፡ እንደተናገረ ፡ እንዲሁ ፡ ስለሚፈጽመው ለነገ ፡ መጨነቄን ፡ ትቼ ፡ ዛሬ ፡ ምስጋናዬን ፡ እሰዋለሁ (፪x) አለቀ ፡ አበቃልኝ ፡ ብዬ ፡ መሰንቆዬንም ፡ ሰቅዬ ተቆርጧል ፡ ባልኩት ፡ ጉዳይ ፡ ከተፍ ፡ አለልኝ ፡ ጌታዬ ባህር ፡ ከፍሎ ፡ ስያሻግረኝ ፡ የረገጥኩትን ፡ ሲያወርሰኝ ስላየሁ ፡ ደግሞ ፡ ደጋግሞ ፡ በድል ፡ ተራራ ፡ ሲያቆመኝ ጌታ ፡ አሰራሩን ፡ አውርቼ ስለማልቸርስ ፡ አውርቼ ተመስገን ፡ ከማለት ፡ በቀር ሌላ ፡ ከቶ ፡ ምን ፡ ልናገር (፪x)

ዳዊት ወልዴ · ሁሉም ዘማሪዎች