Gubae

ኢየሱስ

Eyesus

ዳዊት ወልዴ · መዝሙር ፺ ፩ · 2005

ሥምህን ፡ ሳስጠራ ፡ በዝማሬ በቤትህ ፡ ስኖር ፡ እስከዛሬ አይጠገብም ፡ ከማር ፡ ይጥማል ሥምህ ፡ ከሥሞች ፡ ሁሉ ፡ ይልቃል ያንተን ፡ ውለታ ፡ ነፍሴ ፡ ተረድታ ታከብርሃለች ፡ ጠዋትና ፡ ማታ ታከብርሃለች ፡ ቀንና ፡ ማታ ቀናት ፡ አለፉ ፡ እንደ ፡ ጥላ አምና ፡ ካቻምና ፡ ቀረ ፡ ከኋላ ባሳለፍኳቸው፡ ዘመኞቼ አፍሬ ፡ አላወቅም ፡ አንተን ፡ ጠርቼ የጸና ፡ ክንድ ፡ ነው ፡ መሸሸጊያ ጌታዬ ፡ ስምህ ፡ መጠለያ ካለም ፡ ጥፋት ፡ ማምለጫ ፡ ጥላ አዝ፦ ኢየሱስ ፡ ጌታዬ ፡ አምላኬ እኔ ፡ ከቶ ፡ አልጠግብም ፡ ሥምህን ፡ ጠርቼ ብዙ ፡ ምስጋናህን ፡ ዘምሬ ፡ መስክሬ አባ ፡ አባት ፡ ብሎ ፡ ማነው ፡ ያፈረ አንተን ፡ ተማምኖ ፡ ከስሮ ፡ የቀረ ጻድቅ ፡ ተርቦ ፡ ዘሩ ፡ ሲለምን በታሪክ ፡ የለም ፡ አልሰማንም ለኔስ ፡ ማትረፍ ፡ ነው ፡ ቤትህ ፡ መኖሬ ያንተን ፡ ምስጋና ፡ መዘመሬ ቅዱስ ፡ ሥምህን ፡ መመስከሬ አዝ፦ ኢየሱስ ፡ ጌታዬ ፡ አምላኬ እኔ ፡ ከቶ ፡ አልጠግብም ፡ ሥምህን ፡ ጠርቼ ብዙ ፡ ምስጋናህን ፡ ዘምሬ ፡ መስክሬ (፪x) "ኢየሱስ ፡ ሥምህ ፡ እንደሚፈስ ፡ ዘይት ፡ ነው አጥንትን ፡ ሁሉ ፡ ዘልቆ ፡ እንደሚገባ ነፍስንም ፡ እንደሚያረሰርስ ፡ ቁስልንም ፡ እንደሚፈውስ መልካም ፡ መዓዛ ፡ ያለው ፡ ዘይት ፡ ነው ለክቡር ፡ ሥምህ ፡ እዘምራለሁ" ኢየሱስ ፡ (ኢየሱስ) ፡ ጌታዬ ፡ (ጌታዬ) መድህኔ ፡ (መድህኔ) ፡ አመልክሃለሁ ፡ እኔ (፫x) ሥምህ ፡ ከሥሞች ፡ ሁሉ ፡ በላይ ፡ ነው ከስልጣን ፡ ሁሉ ፡ በላይ ፡ ስልጣን ፡ ያለው በምስጋና ፡ ቃል ፡ እጠራሃለሁ ፡ ጠላቶቼን ፡ እረግጣለሁ (፫x) ጌታዬ ፡ ሥምህ ፡ መሸሸጊያ ከዓለም ፡ ጥፋት ፡ ማምለጫ ፡ ጥላ

ዳዊት ወልዴ · ሁሉም ዘማሪዎች