እኔ የማመልከው
Enie Yemamelkew
ዳዊት ወልዴ · መዝሙር ፺ ፩ · 2005
የጌታን ፡ ውለታ ፡ በምን ፡ እመልሳለሁ ዘላለም ፡ ላመልከው ፡ ቃል ፡ ገብቻለሁ የአምላኬን ፡ ውለታ ፡ በምን ፡ እመልሳለሁ ዘላለም ፡ ላመልከው ፡ ቃል ፡ ገብቻለሁ ችግረኛን ፡ የሚታደግ ፡ የቆሰለን ፡ የሚፈውስ ለታመነው ፡ ፈጥኖ ፡ የሚደርስ ፡ ሥሙ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ማዕበሉን ፡ አሳለፈኝ ፡ ወጀቡንም ፡ አሻገረን እጄን ፡ ይዞ ፡ እየመራ ፡ እዚህ ፡ አደረሰኝ አዝ:- እኔ ፡ የማመልከው ፡ ጌታዬ አባት ፡ ወንድም ፡ ጓደኛዬ ፡ የጸና ፡ ስሙ ፡ መሸሸግያዬ በፍቅሩ ፡ ተማርኬያለሁ ፡ ፍቅጄ ፡ አመልከዋለሁ ለዘላለም ፡ ለእርሱ ፡ እገዛለሁ (፪x) ያን ፡ ፈተና ፡ የገነነ ፡ እንደተራራ ፡ የሆነ የአምላኬን ፡ ስም ፡ ስጠራበት ፡ እንደ ፡ ጉም ፡ ተነነ የባሕሩም ፡ ወጀብ ፡ ከብዶ ፡ ነፍሴን ፡ በሌት ፡ አስጨንቋት ግን ፡ ጌታዬ ፡ ምን ፡ ተስኖት ፡ ተረማመደበት አዝ:- እኔ ፡ የማመልከው ፡ ጌታዬ አባት ፡ ወንድም ፡ ጓደኛዬ ፡ የጸና ፡ ስሙ ፡ መሸሸግያዬ በፍቅሩ ፡ ተማርኬያለሁ ፡ ፈቅጄ ፡ አመልከዋለሁ ለዘላለም ፡ ለእርሱ ፡ እገዛለሁ ፡ (፪x) የጌታን ፡ ውለታ ፡ በምን ፡ እመልሳለሁ ዘላለም ፡ ላመልከው ፡ ቃል ፡ ገብቻለሁ የአምላኬን ፡ ውለታ ፡ በምን ፡ እመልሳለሁ ዘላለም ፡ ላመልከው ፡ ቃል ፡ ገብቻለሁ እግዚአብሔር ፡ እረኛዬ ፡ የማይተኛ ፡ ጠባቂዬ በክፉ ፡ ቀን ፡ ማምለጫዬ ፡ ሥሙ ፡ መከታዬ ይመራኛል ፡ አምነዋለሁ ፡ እርሱ ፡ ይግዛኝ ፡ እገዛለሁ እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ መልካም ፡ አባት ፡ ወዴት ፡ አገኛለሁ አዝ:- እኔ ፡ የማመልከው ፡ ጌታዬ አባት ፡ ወንድም ፡ ጓደኛዬ ፡ የጸና ፡ ስሙ ፡ መሸሸግያዬ በፍቅሩ ፡ ተማርኬያለሁ ፡ ፍቅጄ ፡ አመልከዋለሁ ለዘላለም ፡ ለእርሱ ፡ እገዛለሁ ፡ (፬x)

