Gubae

የራሴ ነገር ስላልጠቀመኝ

Yerasie Neger Selalteqemegn

ዳዊት ሞላልኝ · ተባረረ

አዝ፦ የራሴ ፡ ነገር ፡ ስላልጠቀመኝ ዋጋ ፡ ተምኜ ፡ ወጥቻለሁኝ ጌታን ፡ ማገልገል ፡ ትርፍ ፡ አለውና ጥማዱን ፡ ስበር ፡ ስበር ፡ ውጣና የእኔ ፡ የራሴ ፡ ባልሆነ ፡ ነገር ብዙ ፡ ቆየሁኝ ፡ ያኔ ፡ ስቸገር ዛሬ ፡ ዛሬማ ፡ በራልኝና ድንቁን ፡ ራዕይ ፡ አየሁኝና ሁሉንም ፡ ነገር ፡ ለጌታ ፡ ትቼ እፎይ ፡ አረፍኩኝ ፡ ተማቻችቼ (፬x) አዝ፦ የራሴ ፡ ነገር ፡ ስላልጠቀመኝ ዋጋ ፡ ተምኜ ፡ ወጥቻለሁኝ ጌታን ፡ ማገልገል ፡ ትርፍ ፡ አለውና ጥማዱን ፡ ስበር ፡ ስበር ፡ ውጣና ታማኝ ፡ አድርጐ ፡ ስለቆጠረኝ ለአገልግሎቱ ፡ ጌታ ፡ የሾመኝ ሞኞች ፡ ቢነቅፉኝ ፡ ቢዘብቱብኝ ትቼ ፡ የመጣሁ ፡ ባሪያው ፡ እኮ ፡ ነኝ እየታገሰ ፡ ብርቱ ፡ የሚያደርገው የጌታ ፡ መንፈስ ፡ በላዬ ፡ ላይ ፡ ነው (፬x) አዝ፦ የራሴ ፡ ነገር ፡ ስላልጠቀመኝ ዋጋ ፡ ተምኜ ፡ ወጥቻለሁኝ ጌታን ፡ ማገልገል ፡ ትርፍ ፡ አለውና ጥማዱን ፡ ስበር ፡ ስበር ፡ ውጣና ከአባቴ ፡ ቤት ፡ አስወጣኝ ፡ ጌታ ወዳሳየኝ ፡ ሄድኩ ፡ ሳላመነታ እርሱን ፡ ታምኜ ፡ ስለወጣሁኝ እረሃቡ ፡ ጸና ፡ ጥሬ ፡ ስላለኝ ዘርህ ፡ እንደአሸዋ ፡ ይበዛል ፡ እንዳለው ቃሉን ፡ ፈጸመው ፡ ተዓምረኛ ፡ ነው (፬x) አዝ፦ የራሴ ፡ ነገር ፡ ስላልጠቀመኝ ዋጋ ፡ ተምኜ ፡ ወጥቻለሁኝ ጌታን ፡ ማገልገል ፡ ትርፍ ፡ አለውና ጥማዱን ፡ ስበር ፡ ስበር ፡ ውጣና እናት ፡ አባቴ ፡ እረስተውኛል ቸሩ ፡ እግዚአብሔር ፡ ተቀብሎኛል የሁሉ ፡ ታናሽ ፡ የበግ ፡ እረኛ ታላቅ ፡ እያለ ፡ መርጦ ፡ ቀባኛ እርሱ ፡ ሲያጸድቅ ፡ ማን ፡ ይቃወማል መቼ ፡ በቁመት ፡ ልብም ፡ ይታያል (፬x) አዝ፦ የራሴ ፡ ነገር ፡ ስላልጠቀመኝ ዋጋ ፡ ተምኜ ፡ ወጥቻለሁኝ ጌታን ፡ ማገልገል ፡ ትርፍ ፡ አለውና ጥማዱን ፡ ስበር ፡ ስበር ፡ ውጣና

ዳዊት ሞላልኝ · ሁሉም ዘማሪዎች