ትመቸኛለህ
Temechegnaleh
ዳዊት ሞላልኝ · ተባረረ
አዝ፦ ከአንተው ፡ ጋር ፡ ልወዳጅ ከአንተው ፡ ጋር ፡ ልስማማ (፪x) ምን ፡ ያደርግልኛል ፡ ሌላ ፡ ሌላውማ ምን ፡ ያደርግልኛል ፡ ሌላ ፡ ሌላውማ ትመቸኛለህ ፡ ጌታ ፡ አሃሃ ትመችኛለህ ፡ ኢየሱስ ትመቸኛለህ ፡ አሃ (፪x) ወደ ፡ ላይ ፡ ብወጣ ፡ አንተ ፡ በዚያ ፡ አለህ ወደታች ፡ ብወድቅም ፡ ቀድመህ ፡ ትገኛለህ ከአንተ ፡ ተሸሽቶ ፡ ወዴት ፡ ይደረሳል ከአንተው ፡ ተስማምቶ ፡ መኖር ፡ ይሻለኛል አዝ፦ ከአንተው ፡ ጋር ፡ ልወዳጅ ከአንተው ፡ ጋር ፡ ልስማማ (፪x) ምን ፡ ያደርግልኛል ፡ ሌላ ፡ ሌላውማ ምን ፡ ያደርግልኛል ፡ ሌላ ፡ ሌላውማ ትመቸኛለህ ፡ ጌታ ፡ አሃሃ ትመችኛለህ ፡ ኢየሱስ ትመቸኛለህ ፡ አሃ (፪x) መልካም ፡ ለመሰለኝ ፡ በዓይኔ ፡ ላየሁት ፈቃዴን ፡ ለማድረግ ፡ ልቤን ፡ ከሰጠሁት ጌታዬ ፡ ይቅር ፡ በለኝ ፡ አንተን ፡ ለበደልኩት ቤትህ ፡ ይሻለኛል ፡ ሰላም ፡ የሞላበት አዝ፦ ከአንተው ፡ ጋር ፡ ልወዳጅ ከአንተው ፡ ጋር ፡ ልስማማ (፪x) ምን ፡ ያደርግልኛል ፡ ሌላ ፡ ሌላውማ ምን ፡ ያደርግልኛል ፡ ሌላ ፡ ሌላውማ ትመቸኛለህ ፡ ጌታ ፡ አሃሃ ትመችኛለህ ፡ ኢየሱስ ትመቸኛለህ ፡ አሃ (፪x) ወጥቼ ፡ ነበረ ፡ ድርሻዬን ፡ ሰጥተኸኝ ተመልሼ ፡ መጣሁ ፡ ጨርሼው ፡ አልቆብኝ ፊትህ ፡ አልጠቆረ ፡ በርህ ፡ አልተዘጋብኝ አይደለም ፡ እንደልጅ ፡ ባሪያ ፡ አድርገህ ፡ ግዛኝ አዝ፦ ከአንተው ፡ ጋር ፡ ልወዳጅ ከአንተው ፡ ጋር ፡ ልስማማ (፪x) ምን ፡ ያደርግልኛል ፡ ሌላ ፡ ሌላውማ ምን ፡ ያደርግልኛል ፡ ሌላ ፡ ሌላውማ ትመቸኛለህ ፡ ጌታ ፡ አሃሃ ትመችኛለህ ፡ ኢየሱስ ትመቸኛለህ ፡ አሃ (፪x) ለጊዜው ፡ ከሚገኝ ፡ ከኃጢአት ፡ ደስታ ሞት ፡ ከገነነበት ፡ ግርግር ፡ ሁካታ የሰጠኸኝ ፡ ሰላም ፡ የቤትህ ፡ አርካታ በባዶ ፡ ያዘልላል ፡ ስሙ ፡ የእኔ ፡ ጌታ አዝ፦ ከአንተው ፡ ጋር ፡ ልወዳጅ ከአንተው ፡ ጋር ፡ ልስማማ (፪x) ምን ፡ ያደርግልኛል ፡ ሌላ ፡ ሌላውማ ምን ፡ ያደርግልኛል ፡ ሌላ ፡ ሌላውማ ትመቸኛለህ ፡ ጌታ ፡ አሃሃ ትመችኛለህ ፡ ኢየሱስ ትመቸኛለህ ፡ አሃ (፪x)

