ሌላው አልመች አለኝ
Lelaw Alimech Alegn
ዳዊት ሞላልኝ · አትታማ · 2007
ጌታ ልቤ ገብቶ ስላስደነቀኝ ሌላው ሌላውማ አልመች አለኝ ጌታ ልቤ ገብቶ ስላስደነቀኝ ሌላው ሌላውማ አልመች አለኝ/4 ቢያድነኝም ባያድነኝም ሰው ለቀረፀው ፈፅሞ አልሰግድም ቢያድነኝም ባያድነኝም ለውርቁ ምስል ፈፅሞ አልሰግድም አንዴ አጎንብሼ ሳመሰግነው ደግሞ ቀና ስል እርሱ ሌላ ነው እንዴት ልነሳ እዛው ቀረሁኝ መኖር ለምጄ እያመለኩኝ ጌታ ልቤ ገብቶ … ቢያድነኝም ባያድነኝም … ቀንና ለሊት ቢሰገድለት የማይሰለች ክብር አለበት መኖሬን ሳስብ እርሱ ባለበት ሃሴት አደረኩ ነፍሴም ደስ አላት ጌታ ልቤ ገብቶ … ቢያድነኝም ባያድነኝም … ፀሃይዋንና ጨረቃዋን የሚያስፈጉን ልብርሃን በጉ ባለበት አያስፈጉም ስለሚያበራ ለዘላዓለም ጌታ ልቤ ገብቶ … ቢያድነኝም ባያድነኝም … ጊዜያዊ ደስታ ለሚሰጠው ልቤን አልጥልም ለሚጠፋው በዙፋኑ ፀንቶ ለሚኖት ጨክኛለሁኝ እርሱን ለማክበር ጌታ ልቤ ገብቶ … ቢያድነኝም ባያድነኝም …

