ግርም ይለኛል
Gerem Yelegnal
ዳዊት ሞላልኝ · ተባረረ
አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ግርም ፡ ይለኛል (ይለኛል) እግዚአብሔር ፡ ድንቅ ፡ ይለኛል (፪x) መልካም ፡ ነው (መልካም ፡ ነው) መልካም ፡ ነው (፪x) መንገድ ፡ ላይ ፡ ጥሎኝ ፡ አልሄደም ደከመኝ ፡ ሰለቸኝ ፡ አላለም እግዚአብሔር ፡ ትልቅ ፡ ነው ፡ እላለሁ (፬x) ቀንና ፡ ሌሊቱ ፡ ትልቅ ፡ ነህ ፡ ይሉታል መላዕክት ፡ ፍጥረቱ ፡ ሁሉ ፡ ያመልኩታል አባቶች ፡ አምልከው ፡ አክብረውት ፡ አልፈዋል በእኔና ፡ በቤቴ ፡ ጌታ ፡ ይመለካል አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ግርም ፡ ይለኛል (ይለኛል) እግዚአብሔር ፡ ድንቅ ፡ ይለኛል (፪x) መልካም ፡ ነው (መልካም ፡ ነው) መልካም ፡ ነው (፪x) የወደቀን ፡ ይነሳል ፡ ያለው የሳተውን ፡ የሚመልሰው ኢየሱሴን ፡ እወደዋለሁ (፬x) እንደሌዊ ፡ አይደል ፡ እንዴት ፡ ትቶኝ ፡ ያልፋል ልክ ፡ እንደ ፡ ካህኑ ፡ መች ፡ ያፈገፍጋል ደጉ ፡ ጌታ ፡ እየሱስ ፡ እጁን ፡ ይዘረጋል ቁስሌን ፡ በዘይቱ ፡ ቀብቶ ፡ ያነሳኛል አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ግርም ፡ ይለኛል (ይለኛል) እግዚአብሔር ፡ ድንቅ ፡ ይለኛል (፪x) መልካም ፡ ነው (መልካም ፡ ነው) መልካም ፡ ነው (፪x) ላቆም ፡ ነው ፡ አልሰግድም ፡ ብዬ አልቀረሁም ፡ እሳት ፡ ዉስጥ ፡ ተጥዬ ይታመናል ፡ ታማኝ ፡ ነው ፡ ጌታዬ (፬x) ሰባት ፡ እጥፍ ፡ ሲነድ ፡ ወርውረው ፡ ጣሉኝ የአማልክት ፡ አምላክ ፡ እዛው ፡ አገኘኝ ኧረ ፡ እንዴት ፡ ተረፈ ፡ ከእሳት ፡ ያላችሁ ከመከራው ፡ በፊት ፡ እየሱስ ፡ ያግኛቹ አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ግርም ፡ ይለኛል (ይለኛል) እግዚአብሔር ፡ ድንቅ ፡ ይለኛል (፪x) መልካም ፡ ነው (መልካም ፡ ነው) መልካም ፡ ነው (፪x)

