Gubae

እጥላለሁ

Etilalehu

ዳዊት ሞላልኝ · ተባረረ

ጣል ሲለኝ እጥላለሁ ተው ሲለኝ እተዋለሁ/2 የሚረባኝን የሚያውቅልኝን ሾሜዋለው/2 መልካም ነው ያልኩት እኔ የወደድኩት አይረባህም ሲለኝ ከእጄ ላይ ለቀቅኩት እኔ ካሰብኩት ካወኩትም ይልቅ አምላኬ የሚለው ይነው ውብና ድንቅ/2 ጣል ሲለኝ እጥላለሁ ተው ሲለኝ እተዋለሁ/2 የሚረባኝን የሚያውቅልኝን ሾሜዋለው/2 ለአይኔ የማረኝ መብላት ያስጎመጀኝ ሞት ስላለበት ነው እንዳትነካው ያለኝ እኔ ላዩን እንጂ ውስጡን መች አየሁት የዚች አለም ማማር ሞት አለው በውስጡ/2 ጣል ሲለኝ እጥላለሁ ተው ሲለኝ እተዋለሁ/2 የሚረባኝን የሚያውቅልኝን ሾሜዋለው/2 ክፉውን አስጥሎ መልካም የሚሰጠው በምክሩ ግሩም እግዚአብሔር ነው ከኔ አስቀድሞ ስለኔ የሚያውቀው ጌታዬን ሰምቼ ስንቴ ተርፌያለው/2 ጣል ሲለኝ እጥላለሁ ተው ሲለኝ እተዋለሁ/2 የሚረባኝን የሚያውቅልኝን ሾሜዋለው/2 ሙሴን ጠራና በትሩን አስጣለው ለካስ እባብ ነበር አቅፎት የሚዞረው ካባቴ የወረስኩት የጥንት ነው ያልኩት የሚናደፈወን ሸሸው አመለጥኩት/2 ጣል ሲለኝ እጥላለሁ ተው ሲለኝ እተዋለሁ/2 የሚረባኝን የሚያውቅልኝን ሾሜዋለው/2

ዳዊት ሞላልኝ · ሁሉም ዘማሪዎች