Gubae

እንመለስ

Enimeles

ዳዊት ሞላልኝ · አትታማ · 2007

ምን አይነት ልብ ይዘን ምን እየሰራን ነው በአምልኮ ስፍራ ሁሌ ምንገኘው ጠብና ክርክር አለ በኛ መሃል መዘመር ስንጀምር ጌታስ ምን ይለናል ልብን ኩላሊትን የሚመረምረው እርሱ አይታለልም ማንን ነው ምንዋሸው እንመለስ ሁላችንም ቂመኝነት ለኛ አይሆንም ጌታ ቆሞ ይለምናል ስንመለስ ማየት ይሻል አንዱ አንዱን ሲከሰው ሲጥለው ሲተቸው ሲያማው ሲያዋርደው ነው እኮ ነው ሚታየው ሚሰማው እስቲ እኛ እንዋደድ መርገሙን ይስበረው በኛ ጠብ አያምርም ፍቅር ነው የሚያምረው እንመለስ ሁላችንም ቂመኝነት ለኛ አይሆንም ጌታ ቆሞ ይለምናል ስንመለስ ማየት ይሻል አንቀባበልም አገልጋይ ካገልጋይ በጣም ያሳፍራል ስንቆም መድረክ ላይ ይቅር ሳንባባል ታስረን ተቀምጠን ስለፍቅር ሰብከን ፈውስ እንጠብቃለን ፀሎት ብናስረዝም ባርከንም ብንለው አንተ ማን ነህ ያላል ሁሉን አዋቂ ነው እንመለስ ሁላችንም ቂመኝነት ለኛ አይሆንም ጌታ ቆሞ ይለምናል ስንመለስ ማየት ይሻል ወንጌሉን አስቀምጠን ትልቁን ስራችን እየተካሰስን እርስ በእርሳችን ጉዳችን እስቲ እኛ እንታረቅ እንልመድ ማለትን ያለፈው ይረሳ ሁሉም እጁን ያንሳ እንመለስ ሁላችንም ቂመኝነት ለኛ አይሆንም ጌታ ቆሞ ይለምናል ስንመለስ ማየት ይሻል

ዳዊት ሞላልኝ · ሁሉም ዘማሪዎች