እግዚአብሔር ዘመዴ
Egziabher Zemede
ዳዊት ሞላልኝ · አትታማ · 2007
ዘማሪው ሲዘምር እጁን ሲዘረጋ ያደረገለትን በቅኔ ሲያወጋ እኔም ተስማምቼ መዘመር ጀመርኩኝ እግዚአብሔር ዘመዴ ዘመዴ ነው አልኩኝ እግዚአብሔር ዘመዴ አይደለም ወይ/4 ባለቅኔዎች ዘመሩለት እግዚአብሔር ዘመዳችን ነው አሉ/2 ታዲያ እኔስ ምነው ብዘምር ቅኔና በገናን ብደረድር ሰባኪው ሲሰብክ ጌታን ሲተርከው ለኔ እንደሞተ ፍቅር ግድ እንዳለው እኔም ተደንቄ መስበኬን ጀመርኩኝ እየሱስ ያድናል ያድናል እያልኩኝ እየሱስ ያድናል እያልኩኝ/4 ባለቅኔዎች ዘመሩለት እግዚአብሔር ዘመዳችን ነው አሉ/2 ታዲያ እኔስ ምነው ብዘምር ቅኔና በገናን ብደረድር ውለታው እንዴት ይረሳል/2 እንዴት ይረሳል ፍቅሩ እንዴት ይረሳል/2 እንዴት ይረሳል ማዳኑ እንዴት ይረሳል/2 እንዴት ይረሳል ኧረ እንዴት/3 ይረሳል ይደርደር በገና ይደርደር በገና እኔም እንደዳዊት መዝሙር አለኝና ይደርደር በገና ይደርደር በገና ከሞት ያስመለጠኝ እየሱስ ነውና

