Gubae

አንተማ አትታማ

Antema Atitama

ዳዊት ሞላልኝ · አትታማ · 2007

ቀኑ ፡ ሲከፋ ፡ ጊዜው ፡ ሲረዝም ጌታ ፡ ትቶኛል ፡ ብዬ ፡ ስቆዝም በጊዜው ፡ ደርሰህ ፡ ውብ ፡ አድርገሃል ድንቅ ፡ አድራጊ ፡ ነህ ፡ አንተን ፡ ማን ፡ ያምሃል አዝ፦ አንተማ (፫x) ፡ አትታማ (፪x) ጌታማ ፡ አይታማ (፬x) ተስፋው ፡ ሲዘገይ ፡ ሲጨልምብኝ ብዬው ፡ ነበረ ፡ ጌታን ፡ ግደለኝ ሌቱ ፡ ሲነጋ ፡ ሁሉም ፡ ሲቀየር ብዬ ፡ ፀለይኩ ፡ እድሜዬን ፡ ጨምር አዝ፦ አንተማ (፫x) ፡ አትታማ (፪x) ጌታማ ፡ አይታማ (፬x) የታመንንበት ፡ ተስፋ ፡ ያረግነው ሞተብን ፡ ብለው ፡ አዝነው ፡ ጠውልገው ድንገት ፡ ተገልጦ ፡ መካከላቸው በሶስተኛው ፡ ቀን ፡ አሳፈራቸው አዝ፦ አንተማ (፫x) ፡ አትታማ (፪x) ጌታማ ፡ አይታማ (፬x) ለሚበላና ፡ ለሚጠታዉ እንዴት ፡ ይታማል ፡ ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው ንፋስ ፡ ሳይታይ ፡ ዝናብም ፡ ሳይኖር ምንጭን ፡ ያፈልቃል ፡ ከደረቅ ፡ ምድር አዝ፦ አንተማ (፫x) ፡ አትታማ (፪x) ጌታማ ፡ አይታማ (፬x)

ዳዊት ሞላልኝ · ሁሉም ዘማሪዎች