Gubae

አምልኮ ለጌታ ነው

Amleko Legieta New

ዳዊት ሞላልኝ · ተባረረ

አዝ፦ እወድሀለው ፡ ብዬ ፡ ለአንተ ፡ ብዘምር ማነው ፡ ሚከራከር ፡ ማነው ፡ ሚለው ፡ ቅር (፫x) ይወራ ፡ የጌታዬ ፡ ሥራ ይወራ ፡ የአምላኬ ፡ ሥራ (፪x) ሰው ፡ ዝም ፡ ብሎ ፡ ይከራከራል ጌታውን ፡ ለማምለክ ፡ ጥቅስ ፡ ያወጣጣል አንዱ ፡ እንዲህ ፡ ነው ፡ ሲል ፡ ሌላው ፡ እንዲያ ፡ ይላል አምልኮ ፡ ለጌታ ፡ ነው ፡ ሰውን ፡ ምን ፡ ነክቶታል በመንፈስ ፡ ይሁን ፡ እንጂ ፡ እየሱስ ፡ ተመችቶታል (የእኔ ፡ ጌታ) አምላኬ ፡ ተቀብሎታል እየሱስ ፡ ተመችቶታል (ኢየሱስ) ፡ አምላኬ ፡ ተቀብሎታል አዝ፦ እወድሀለው ፡ ብዬ ፡ ለአንተ ፡ ብዘምር ማነው ፡ ሚከራከር ፡ ማነው ፡ ሚለው ፡ ቅር (፫x) ይወራ ፡ የጌታዬ ፡ ሥራ ይወራ ፡ የአምላኬ ፡ ሥራ (፪x) ጡት ፡ ከሚጠቡት ፡ ከህፃናቱ ምስጋናን ፡ ለእርሱ ፡ ማዘጋጀቱ ገብቶት ፡ እኮ ፡ ነው ፡ አይደለም ፡ በከንቱ አምልኮ ፡ ምስጋናቸው ፡ ገብቷል ፡ ፀባኦቱ ለእኛ ፡ አይግባን ፡ እንጂ ፡ ወዶታል ፡ ይሄ ፡ ክንዴ ፡ ብርቱ ወዶታል ፡ እየሱስ ፡ ብርቱ (፫x) አዝ፦ እወድሀለው ፡ ብዬ ፡ ለአንተ ፡ ብዘምር ማነው ፡ ሚከራከር ፡ ማነው ፡ ሚለው ፡ ቅር (፫x) ይወራ ፡ የጌታዬ ፡ ሥራ ይወራ ፡ የአምላኬ ፡ ሥራ (፪x) ብልቃጡን ፡ ሰብራ ሽቶ ፡ አፈሰሰች ድሮ ፡ በሚያውቋት ፡ እየተተቸች የጌታዋን ፡ እግር ፡ መሳሟን ፡ ቀጠለች እየሱስ ፡ ተደነቀ ፡ በሰላም ፡ ሂጂ ፡ አላት በተቺዎቿ ፡ ፊትም ፡ ጌታዬ ፡ መሰከረላት (የእኔ ፡ ጌታ) አባቴ ፡ ልክ ፡ ነሽ ፡ አላት ኢየሱስ (ኢየሱስ) ፡ መሰከረላት ፡ አባቴ ፡ መሰከረላት አዝ፦ እወድሀለው ፡ ብዬ ፡ ለአንተ ፡ ብዘምር ማነው ፡ ሚከራከር ፡ ማነው ፡ ሚለው ፡ ቅር (፫x) ይወራ ፡ የጌታዬ ፡ ሥራ ይወራ ፡ የአምላኬ ፡ ሥራ (፪x) እኔን ፡ ያዳነኝ ፡ የደሙ ፡ ሚስጥር ገብቶኝ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ የውዴ ፡ ፍቅር ምስጋና ፡ አምልኮዬ ፡ ለጌታዬ ፡ ክብር ንገሥ ፡ በሕይወቴ ፡ ላይ ፡ ክበር ፡ ጌታ ፡ እየሱስ አምልኮ ፡ ለአንተ ፡ ብቻ ፡ ለሌላ ፡ እኔ ፡ አለስቀምስ (ለመላዕክት) ለሌላ ፡ እኔ ፡ አለስቀምስ (ለሰማዕቶት) ለሌላ ፡ እኔ ፡ አለስቀምስ (ለመላዕክት) ለሌላ ፡ እኔ ፡ አለስቀምስ (ለሰማዕቶት አዝ፦ እወድሀለው ፡ ብዬ ፡ ለአንተ ፡ ብዘምር ማነው ፡ ሚከራከር ፡ ማነው ፡ ሚለው ፡ ቅር (፫x) ይወራ ፡ የጌታዬ ፡ ሥራ ይወራ ፡ የአምላኬ ፡ ሥራ (፪x)

ዳዊት ሞላልኝ · ሁሉም ዘማሪዎች