Gubae

አምልኮ ለጌታ ነው

Amleko Legieta New

ዳዊት ሞላልኝ · አትታማ · 2007

እወድሀለው ፡ ብዬ ፡ ለአንተ ፡ ብዘምር ማነው፡ የሚከራከር ፡ ማነው ፡ የሚለው ፡ ቅር ይወራ ፡ የጌታዬ ፡ ሥራ ይወራ ፡ የአምላኬ ፡ ሥራ (፪x) ሰው ፡ ዝም ፡ ብሎ ፡ ይከራከራል ጌታን ፡ ለማምለክ ፡ ጥቅስ ፡ ያወጣጣል አንዱ ፡ እንዲህ ፡ ነው ፡ ሲል ፡ ሌላው ፡ እንዲያ ፡ ይላል አምልኮ ፡ ለጌታ ፡ ነው ፡ ሰውን ፡ ምን ፡ ነክቶታል በመንፈስ ፡ ይሁን ፡ እንጂ ፡ እየሱስ ፡ ተመችቶታል አምላኬ ፡ ተቀብሎታል እወድሀለው ፡ ብዬ ፡ ለአንተ ፡ ብዘምር ማነው፡ የሚከራከር ፡ ማነው ፡ የሚለው ፡ ቅር ይወራ ፡ የጌታዬ ፡ ሥራ ይወራ ፡ የአምላኬ ፡ ሥራ (፪x) ጡት ፡ ከሚጠቡት ፡ ከህፃናቱ ምስጋናን ፡ ለእርሱ ፡ ማዘጋጀቱ ገብቶት ፡ እኮ ፡ ነው ፡ አይደለም ፡ በከንቱ አምልኮ ፡ ምስጋናችን ፡ ገብቷል ፡ ፀባኦቱ ለእኛ ፡ አይግባን ፡ እንጂ ፡ ወዶታል ፡ ይሄ ፡ ክንዴ ፡ ብርቱ ወዶታል ፡ እየሱስ ፡ ብርቱ እወድሀለው ፡ ብዬ ፡ ለአንተ ፡ ብዘምር ማነው፡ የሚከራከር ፡ ማነው ፡ የሚለው ፡ ቅር ይወራ ፡ የጌታዬ ፡ ሥራ ይወራ ፡ የአምላኬ ፡ ሥራ (፪x) ብልቃጡን ፡ ሰብራ ሽቶ ፡ አፈሰሰች ድሮ ፡ በሚያውቋት ፡ እየተተቸች የጌታዋን ፡ እግር ፡ መጠቧን ፡ ቀጠለች እየሱስ ፡ ተደነቀ ፡ በሰላም ፡ ሂጂ ፡ አላት በተቺዎቿ ፡ ፊትም ፡ ጌታዬ ፡ መሰከረላት እወድሀለው ፡ ብዬ ፡ ለአንተ ፡ ብዘምር ማነው፡ የሚከራከር ፡ ማነው ፡ የሚለው ፡ ቅር ይወራ ፡ የጌታዬ ፡ ሥራ ይወራ ፡ የአምላኬ ፡ ሥራ (፪x) እኔን ፡ ያዳነኝ ፡ የደሙ ፡ ሚስጥር ገብቶኝ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ የውዴ ፡ ፍቅር ምስጋና ፡ አምልኮዬ ፡ ለጌታዬ ፡ ክብር እኔስ፡ በሕይወቴ ፡ ላይ ፡ ክበር ፡ ጌታ ፡ እየሱስ አምልኮ ፡ ለአንተ ፡ ብቻ፡ ለሌላ ፡ እኔ ፡ አለስቀምስ ለመላእት ፡ እኔ ፡ አለስቀምስ ለሰማዕታት ፡ እኔ ፡ አለስቀምስ እወድሀለው ፡ ብዬ ፡ ለአንተ ፡ ብዘምር ማነው፡ የሚከራከር ፡ ማነው ፡ የሚለው ፡ ቅር ይወራ ፡ የጌታዬ ፡ ሥራ ይወራ ፡ የአምላኬ ፡ ሥራ (፪x)

ዳዊት ሞላልኝ · ሁሉም ዘማሪዎች