አልቸኩልም
Alchekulim
ዳዊት ሞላልኝ · አትታማ · 2007
አልቸኩልም ረጋ ብዬ ጠብቃለው/2 ሁሉም ነገር ስደርስበት ያኔ ቀላል ነው/2 ቸኩዬ ወጥቼ ምን አግኝቼ አውቃለው ጌታዬን ጠብቄ ሁሉን አግኝቻለው ባለፈው ዘመኔ አወኩ አንድ ነገር ጌታን ከጠበኩት እንደማያሳፍር አልቸኩልም ረጋ ብዬ ጠብቃለው/2 ሁሉም ነገር ስደርስበት ያኔ ቀላል ነው/2 አሁኑኑ አግኝቼ ይዤ ካላየሁት ያልኩትን ያን ነገር ጥሬ አገኘሁት ታምር መስሎ የታየኝ እንዲያ ያጣደፈኝ እጄ ላይ ሲገባ ቀሎብኝ ሰለቸኝ አልቸኩልም ረጋ ብዬ ጠብቃለው/2 ሁሉም ነገር ስደርስበት ያኔ ቀላል ነው/2 እኔ ተጣድፌ ያመጣሁት ነገር አይሁት ከእጄ ላይ ወድቆብኝ ሲሰበር የጠበኩት ያንን የእግዚአብሔርን ነገር ሲመጣም ደስ ይላል ፀንቶ ስለሚኖር አልቸኩልም ረጋ ብዬ ጠብቃለው/2 ሁሉም ነገር ስደርስበት ያኔ ቀላል ነው/2

