Gubae

ዘለዓለም

Zelalem

ዳዊት ጌታቸው · እጠብቅሃለሁ · 2010

ሥራህን ፡ ለመግለፅ ፡ አንደበት ፡ ቢያንሰኝም ከምሥጋና ፡ በቀር ፡ የምለው ፡ የለኝም ሳወራው ፡ እኖራለሁ ፡ እስከ ፡ ለዘለዓለም ያደረከው ፡ ሁሉ ፡ ከልቤ ፡ አይጠፋም ጊዜው ፡ ቢርቅ ፡ ብዙ ፡ ቢያልፍም ከልቤ ፡ ውስጥ ፡ ከቶ ፡ አይጠፋም ከዚህ ፡ የሚበልጥ ፡ ፍቅር ፡ የለም ትዝ ፡ ይለኛል ፡ እስከ ፡ ዘለዓለም አዝ:- ዘለዓለም ፡ አይጠፋም ፡ ኢየሱስ ፡ ፍቅርህ ያደረከው ፡ ሁሉ ፡ ዉለታህ ከቶ ፡ አልረሳውም ፡ ታትሟል ፡ በልቤ የዘለዓለም ፡ ፍቅሬ ፡ ነህ ፡ ወዳጄ መገረፍ ፡ መድማትህ ፡ ለእኔ ፡ መሞትህ ከጥፋት ፡ እንዳመልጥ ፡ ከክብርህ ፡ መውረድህ ከተወጋው ፡ ጐንህ ፡ የፈሰሰው ፡ ደምህ ዘወትር ፡ ትዝ ፡ ይለእኛል ፡ ኢየሱስ ፡ መከራህ የመስቀሉ ፡ ዉለታህ ፡ ለእኔ ፡ ትልቅ ፡ ትዝታ ፡ ነው ፡ መድህኔ ሕይወትን ፡ ሰጥተህ ፡ አድነኀኛል ፍቅርህ ፡ ከልቤ ፡ ወስጥ ፡ እንዴት ፡ ይጠፋል አዝ:- ዘለዓለም ፡ አይጠፋም ፡ ኢየሱስ ፡ ፍቅርህ ያደረከው ፡ ሁሉ ፡ ዉለታህ ከቶ ፡ አልረሳውም ፡ ታትሟል ፡ በልቤ የዘለዓለም ፡ ፍቅሬ ፡ ነህ ፡ ወዳጄ (፪x) ዓይኔ ፡ ሌላ ፡ ከቶ ፡ አያይም ምርጫዬ ፡ ነህ ፡ ለዘለዓለም ፍቅርህ ፡ ልቤን ፡ ውስጥ ፡ ሰርጾ ፡ ገብቷል ማንም ፡ ሳይቀይረው ፡ ይኖራል

ዳዊት ጌታቸው · ሁሉም ዘማሪዎች