ቀን
Qen
ዳዊት ጌታቸው · እጠብቅሃለሁ · 2010
ድግስ ፡ አዘጋጅቷል ፡ ንጉሡ ፡ በይፋ ያላወቀ ፡ ሁሉ ፡ በከንቱ ፡ እንዳይለፋ ለሚገባው ፡ ሁሉ ፡ በእውነተኛው ፡ በር መንገዱ ፡ አንድ ፡ ነው ፡ የለም ፡ ከእርሱ ፡ በቀር ልብሳችንን ፡ አጥበን ፡ አጽድተን ፡ በደሙ ተግተን ፡ እንጠብቀው ፡ ቅርብ ፡ ነው ፡ ሰዓቱ አዝ:- አንድ ፡ ቀን ፡ አምላኬን ፡ እገናኘዋለሁ ሚያየኝን ፡ ጌታ ፡ እኔ ፡ አየዋለሁ በደስታ ፡ ሁሌ ፡ በፊቱ ፡ እዘምራለሁ ዘለዓለም ፡ ከእርሱ ፡ ጋር ፡ እኖራለሁ እንዴት ፡ ግሩም ፡ ቀን ፡ ነው ፡ ጌታን ፡ የማይበት ከዚህች ፡ ዓለም ፡ ስቃይ ፡ ከቶ ፡ የማርፍበት ኢየሱስ ፡ ይመጣል ፡ ታጅቦ ፡ በክብር አብረን ፡ እንሄዳለን ፡ ልንኖር ፡ ከእርሱ ፡ ጋር አዝ:- አንድ ፡ ቀን ፡ አምላኬን ፡ እገናኘዋለሁ ሚያየኝን ፡ ጌታ ፡ በዐይኔ ፡ አየዋለሁ ከደመና ፡ ከፍ ፡ ካለው ፡ በላይ ፡ እሄዳለው ዘለዓለም ፡ ከእርሱ ፡ ጋር ፡ እኖራለሁ እንዴት ፡ ብሩህ ፡ ቀን ፡ ነው ፡ ያን ፡ ቀን አብረን ፡ እንሄዳለን

