ናፍቃለሁ
Nafeqalehu
ዳዊት ጌታቸው · እጠብቅሃለሁ · 2010
ኃያላን ፡ ሲነሱ ፡ እርስ ፡ በዕርሳቸው ምድር ፡ ስትናወጥ ፡ ግራ ፡ ሲገባቸው ቀኑ ፡ ሲደርስ ፡ ግን ፡ አንተ ፡ ስትመጣ ያን ፡ ጊዜ ፡ ያበቃል ፡ የዚች ፡ ዓለም ፡ ጣጣ አዝ:- ናፍቃለሁ ፡ ያንን ፡ ቀን ፡ ላይ ፡ ሁልጊዜ ፡ እሮጣለሁ የተሰቀለውን ፡ የሞተውን ፡ የተነሳውን ፡ ላየው የመላዕክት ፡ ድምፅ ፡ ዝማሬያቸው ፡ ከሩቁ ፡ ይሰማኛል የምጠብቀው ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ መምጫው ፡ ጊዜ ፡ ደርሷል ሁሉ ፡ በሁሉ ፡ ነው ፡ ምንም ፡ አይጐድለንም በሰማይ ፡ ቤት ፡ ስቃይ ፡ ጉስቁልና ፡ የለም እንዘምራለን ፡ ዘለዓለም ፡ በደስታ ለይሁዳ ፡ አንበሳ ፡ ሞትን ፡ ድል ፡ ለነሳ አዝ:- ናፍቃለሁ ፡ ያንን ፡ ቀን ፡ ላይ ፡ ሁልጊዜ ፡ እሮጣለሁ የተሰቀለውን ፡ የሞተውን ፡ የተነሳውን ፡ ላየው የመላዕክት ፡ ድምፅ ፡ ዝማሬያቸው ፡ ከሩቁ ፡ ይሰማኛል የምጠብቀው ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ መምጫው ፡ ጊዜ ፡ ደርሷል ጌታ ፡ ሲመጣ ፡ በመላእክት ፡ ታጅበን ከሙሽራው ፡ ጋር ፡ ልንኖር ፡ አብረን ፡ እንሄዳለህ የሚያሰጋን ፡ የለም ፡ ዕዳችን ፡ ሁሉ ፡ ተከፍሏል በነጽነት ፡ ልንኖር ፡ ከእርሱ ፡ ጋር ዳግመኛ ፡ በክብር ፡ ይመጣል (፪x) ጌታ ፡ ሲመጣ ፡ በመላእክት ፡ ታጅበን

