ለሥምህ
Lesemeh
ዳዊት ጌታቸው · እጠብቅሃለሁ · 2010
ትዝ ፡ ይለኛል ፡ የማልረሳው ፡ ብዙ ፡ ታሪክ ፡ አለኝ ራሴን ፡ አውቃለሁ ፡ ማንነቴን ፡ ከየት ፡ እንዳነሳኝ ዛሬ ፡ ላይ ፡ ቆሜ ፡ ሳስታውሰው ፡ ያለፈውን ፡ ሁሉ ስታግዘኝ ፡ ያዩ ፡ ዓይኖቼ ፡ በእንባ ፡ ይሞላሉ ክብር ፡ ለሥምህ ፡ ይሁን ፡ እዚህ ፡ አደረስከኝ ቀን ፡ ይመሻል ፡ ደግሞ ፡ ይነጋል ሁሉም ፡ ነገር ፡ ያልፋል ትዝታውን ፡ ግን ፡ ለመርሳት ፡ ከቶ ፡ እንዴት ፡ ይቻላል ባትደርስልኝ ፡ ባትዘረጋው ፡ የምህረት ፡ እጅህን ሳስበው ፡ እፈራለሁ ፡ መጨረሻዬን ክብር ፡ ለሥምህ ፡ ይሁን ፡ እዚህ ፡ አደረስከኝ በደስታ ፡ በሀዘኔ ፡ ከቶ ፡ ሳትለየኝ ተሸከምከኝ ፡ እዚህ ፡ አደረስከኝ ቀኖቹ ፡ ቢያልፉ ፡ መቼም ፡ አይረሳኝ ዛሬ ፡ ቆሜ ፡ ዘምረዋለሁ ፡ ለእኔ ፡ ያደረከው ፡ ብዙ ፡ ነው አንዳች ፡ የለም ፡ ከእኔ ፡ ነው ፡ የምለው አመሰግንሃለሁ ሁሉም ፡ አልፎ ፡ ዛሬ ፡ ቆሜያለሁ ከአንተ ፡ የተነሳ ፡ እዚህ ፡ አለሁ ስለነገ ፡ እንዴት ፡ እፈራለሁ ሕይወቴ ፡ በእጅህ ፡ ነው

