ሁኔታዎችን
Hunietawochin
ዳዊት ጌታቸው · እጠብቅሃለሁ · 2010
ሁኔታዎችን ፡ አይቼ ፡ ተመስገን ፡ አልልህም ያሰብኩት ፡ ባይሳካ ፡ አፌን ፡ አላበላሽም እግዚአብሔር ፡ አንተ ፡ በእውነት ፡ ጻድቅ ፡ ነህ የሚሳንህ ፡ አንዳች ፡ የለም ይሆናል ፡ አይሆን ፡ ብዬ ፡ በዚህ ፡ አልገመግምህም ለባህር ፡ ገደብን ፡ ሰጠህ ከዚህ ፡ አትለፍ ፡ ብለህ ፀሀይም ፡ በማለዳ ፡ በቃልህ ፡ ያጸና አንተ ፡ ስትናገር ፡ የማይሆን ፡ የቱ ፡ ነው ሁኔታን ፡ አይቼ ፡ ክፉ ፡ አይወጣኝም ፡ ሁሉም ፡ ነገር ፡ ለበጎ ፡ ነው አንተ ፡ ለእኔ ፡ ያለህ ፡ አላማ ፡ መልካም ፡ ነው ፡ ለዘለዓለም በሞት ፡ ጥላ ፡ ውስጥ ፡ ብራመድ ፡ ክፉውን ፡ እኔ ፡ አልፈራም ብታድነኝ ፡ ባታድነኝም ፡ ብትሰጠኝ ፡ ብትነሳኝም አምልኮ ፡ ስራዬ ፡ እንጂ ፡ የሕይወቴ ፡ ጊዜያዊው ፡ ስሜት ፡ አይደለም ሁሉን ፡ ታደርግ ፡ ዘንድ ፡ ቻይ ፡ ነህ ፡ በስራህ ፡ አትሳሳትም አማካሪ ፡ አትፈልግ ፡ የትኛው ፡ ነገር ፡ አቅቶህ ስለዚህ ፡ ራሴን ፡ እንቃለው ፡ በምትሰራው ፡ ስራ ምህረትህ ፡ ለእኔ ፡ ይብዛልኝ ለሃጥያቴ ፡ ከማውቅህ ፡ በላይ ፡ ነህና

