Gubae

ጌታ ሆይ

Gieta Hoy

ዳዊት ጌታቸው · እጠብቅሃለሁ · 2010

ሽክሜን ፡ እና ጭንቀቴን በፊትህ ፡ ይዤ ፡ እቀርባለሁ ያለፈው ፡ ይበቃኛል መለወጥን ፡ እሻለሁ አዝ:- ጌታ ፡ ሆይ ፡ የልመናዬን ፡ ቃል ፡ ስማ ፀሎቴንም ፡ መልስልኝ ፡ እጅህን ፡ ዘርግተህ ፡ ታደገኝ በእራሴ ፡ ብዙ ፡ ደክሜያለሁ ፡ ስለፋ የማላውቀውን ፡ ተስፋ ፡ ዕድሜዬን ፡ ሙሉ ፡ ስለፋ የአንተን ፡ የልብህን ፡ ሃሳብ ፡ እየፈጸምኩኝ ፡ መኖር ፡ እሻለሁ ከዚህች ፡ ዓለም ፡ ከንቱ ፡ ነገር ፡ ዐይኔንም ፡ አነሳዋለሁ ዋጋ ፡ አለውና ፡ የከበረ ፡ እርሱን ፡ ለመያዝ ፡ እዘረጋለሁ ከእንግዲህ ፡ በቀረኝ ፡ እድሜ ፡ ክብርህን ፡ ማየት ፡ እሻለሁ ባለማስተዋል ፡ የሰበሰብኩት ከንቱ ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ ለካስ ፡ ያከማቸሁት ክፋቴን ፡ ሁሉ ፡ ዞር ፡ ብዬ ፡ ሳየው እራሴን ፡ ስወቅስ ፡ ደግሞ ፡ እገኛለሁ ደግሞ ፡ እንደገና ፡ ነግቶልኝ ፡ ስሮጥ አንድ ፡ ዐይነት ፡ ሕይወት ፡ የማይለወጥ ይህ ፡ ከንቱ ፡ ኑሮ ፡ ብዙ ፡ ደከመኝ አሁን ፡ ግን ፡ በቃኝ ፡ ባክህ ፡ ለውጠኝ አዝ:- ጌታ ፡ ሆይ ፡ የልመናዬን ፡ ቃል ፡ ስማ ፀሎቴንም ፡ መልስልኝ ፡ እጅህን ፡ ዘርግተህ ፡ ታደገኝ በእራሴ ፡ ብዙ ፡ ደክሜያለሁ ፡ ስለፋ የማላውቀውን ፡ በተስፋ ፡ ዕድሜዬን ፡ ሙሉ ፡ ስለፋ

ዳዊት ጌታቸው · ሁሉም ዘማሪዎች