በምህረቱ
Bemeheretu
ዳዊት ጌታቸው · እጠብቅሃለሁ · 2010
ኃጥያተኛ ፡ ነበርኩ ፡ ዓለም ፡ ጉድ ፡ ያለልኝ ለሰራሁት ፡ በደል ፡ ሞት ፡ የፈረዱብኝ ገበናዬን ፡ ገልጠው ፡ እየገፈተሩኝ ለፍርድ ፡ አቀረቡኝ ፡ በድንጋይ ፡ ሊወግሩኝ ዳኛው ፡ ግን ፡ ስለ ፡ እኔ ፡ በእውነት ፡ አዘነልኝ ውስጡን ፡ እያወቀ ፡ ለእኔ ፡ ፈረደልኝ ከከሳሾቼ ፡ እጅ ፡ በጥበብ ፡ አስጥሎኝ በእኔ ፡ ፋንታ ፡ እርሱ ፡ ሞቶ ፡ ከፈለልኝ አዝ:- በምህረቱ ፡ ዛሬ ፡ ቆሜያለሁ ስለ ፡ እኔ ፡ ሞቶ ፡ እኔ ፡ ድኛለሁ ነፍሴን ፡ ከሚሹ ፡ ከከሳሾቼ ማምለጥ ፡ ችያለሁ ፡ ምህረት ፡ አግኝቼ ስለ ፡ እኔ ፡ ሞቶ ፡ እኔ ፡ ድኛለሁ የምህረቱ ፡ ብዛት ፡ ከባሕር ፡ ይጠልቃል ስለኀጢያተኛው ፡ በእውነት ፡ ግድ ፡ ይለዋል እርሱ ፡ ነው ፡ ዳኛዬ ፡ የሆነኝ ፡ ጠበቃ ቀድሞ ፡ የታደገኝ ፡ ሕይወቴ ፡ ሲያበቃ ከሳሾቼ ፡ ሁሉ ፡ ድንጋያቸውን ፡ ጥለው ወደ ፡ ኋላ ፡ ሸሹ ፡ ህሊና ፡ ወቅሷቸው ስራዬን ፡ ሰርቶታል ፡ አሁን ፡ ነጻ ፡ ሰው ፡ ነኝ ላዳነኝ ፡ ኢየሱስ ፡ እዘምራለሁኝ አዝ:- በምህረቱ ፡ ዛሬ ፡ ቆሜያለሁ ስለ ፡ እኔ ፡ ሞቶ ፡ እኔ ፡ ድኛለሁ ነፍሴን ፡ ከሚሹ ፡ ከከሳሾቼ ማምለጥ ፡ ችያለሁ ፡ ምህረት ፡ አግኝቼ ዋጋዬ ፡ ይሄ ፡ ነው በእርሱ ፡ ደም ፡ ታጥቤያለሁ ፡ እኔ ፡ ድኛለሁ ስለ ፡ እኔ ፡ ሞቶ ፡ አድኖኛል በእርሱ ፡ ቁስል ፡ ተፌውሻለሁ ነፍሴን ፡ ከሚሹ ፡ ከአዳኝ ፡ ወጥመድ አስመለጠኝ ፡ አኔን ፡ አዳነኝ ዛሬ ፡ በደስታ ፡ ዘምራለሁ በእርሱ ፡ ቁስል ፡ እኔ ፡ ድኛለሁ ፍቅሩን ፡ እያሰብኩ ፡ በፊቱ ፡ ዘምራለሁ ከሞት ፡ አፍ ፡ ከጫፍ ፡ ላይ ፡ አውጥቶኛልና ታሪኬን ፡ አወራለሁ ምህረቱን ፡ እያሰብኩ ፡ በፊቱ ፡ ዘምራለሁ ለነፍሴ ፡ መዳን ፡ ሆኖላታልና ሥሙን ፡ እባርካለሁ (፪x)

