Gubae

በማዕበል ውስጥ ሆኖ

Bemaebel Wust Hono

ዳዊት ጌታቸው · እጠብቅሃለሁ · 2010

በማዕበል ውስጥ ሆኖ ከአንተ ጋራ መሄድ ነው መሄድ ነው በወጀብም መሃል ከአንተ ጋራ መሄድ ነው መሄድ ነው በባሕር ላይ ሆኖ ከአንተ ጋራ በሚያስተጋባው ተሽመድምዶ መቅረት ለምንድነው ግራ እንደገባው ከቶ ለምን ይሆን ከአንተ ጋራ የምንፈራው የዘወትር ልመና አሃሃሃ የምናደርሰው ጌታ ሆይ እባክህ ዓይኖቻችንን ክፈተው በእውነት ከእኛ ጋራ መሆንህን እንድናውቀው (2x) አንተ እያለህ ሁሉን ቻይ ከጐናችን እንፈራለን ወጀቡን እያየን እምነታችንም በሁኔታዎች ጥለን ወየሁ ጠፋን እያልን እንጮሃለን (ከእንግዲህ ከአንተ ጋር ቀና ብለን እንሄዳለን ወጀቡን እንፈራውም በስምህ እንረግጠዋለን) 2x ለአእዋፍ ሁሉ አሃ የምታጠግብ ነህ ለእኛ ለልጆችህ አሃ እንዴት ትነሳለህ ብታደርግ ሁልጊዜ አሃ መች እናውቅሃለን ስለሚቀጥለው ደግሞ ብዙ እናስባለን ጌታ አንተን ብናይ አሃ ይህ ባልሆነ በእኛ እምነት ጨምርልን ጌታ ሆይ አናውቅህምና ጌታ ሆይ እባክህ ዓይኖቻችንን ክፈተው በእውነት ከእኛ ጋራ መሆንህን እንድናውቀው (2x) አንተ እያለህ ሁሉን ቻይ ከጐናችን እንፈራለን ወጀቡን እያየን እምነታችንም በሁኔታዎች ጥለን ወየሁ ጠፋን እያልን እንጮሃለን (ከእንግዲህ ከአንተ ጋር ቀና ብለን እንሄዳለን ወጀቡን እንፈራውም በስምህ እንረግጠዋለን) 2x

ዳዊት ጌታቸው · ሁሉም ዘማሪዎች