ባሻገር
Bashager
ዳዊት ጌታቸው · እጠብቅሃለሁ · 2010
ከአድማስ ፡ ባሻገር ፡ ከዓይናችን ፡ የራቀ ከሩቁ ፡ ስናየው ፡ ሰማዩ ፡ ወደቀ ነገር ፡ ግን ፡ የአራቱም ፡ መጨረሻ ፡ አንተ ፡ ነህ ፍጥረት ፡ እጅህ ፡ ላይ ፡ ነው ፡ ምን ፡ ያህል ፡ ትልቅ ፡ ነህ አዝ:- በእውነት ፡ እኛም ፡ አናውቅህ ፡ እግዚአብሔር ፡ ትልቅ ፡ ነህ ከአእምሮአችን ፡ በላይ ፡ ጥልቅ ፡ ነው ፡ ችሎታህ ሥራዎችን ፡ ሁሉ ፡ ስለ ፡ አንተ ፡ አወሩ ይሁን ፡ ስትላቸው ፡ ሆኑ ፡ ፍጥረታት ፡ በሙሉ ክብር ፡ ለሥምህ ፡ ይሁን ንፋስ ፡ በምድር ፡ ላይ ፡ እንዴት ፡ ይበተናል የበረዶው ፡ ክምር ፡ ማን ፡ አጥቦ ፡ አፅድቶታል ምድርን ፡ ስትሰራ ፡ ማን ፡ ነበረ ፡ አብሮህ እንዲህ ፡ አድርግ ፡ ብሎህ ፡ ማንስ ፡ አማከረህ አዝ:- በእውነት ፡ እኛም ፡ አናውቅህ ፡ እግዚአብሔር ፡ ትልቅ ፡ ነህ ከአእምሮአችን ፡ በላይ ፡ ጥልቅ ፡ ነው ፡ ችሎታህ ሥራዎችን ፡ ሁሉ ፡ ስለ ፡ አንተ ፡ አወሩ ይሁን ፡ ስትላቸው ፡ ሆኑ ፡ ፍጥረታት ፡ በሙሉ ክብር ፡ ለሥምህ ፡ ይሁን ኪሩቤል ፡ ሱራፌል ፡ የሚያመሰግኑህ እልፍ ፡ እእላፍ ፡ መላእክቶች ፡ ወድቀው ፡ የሚሰግዱልህ በእውነት ፡ አንተ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነህ (፪x) አዝ:- በእውነት ፡ እኛም ፡ አናውቅህ ፡ እግዚአብሔር ፡ ትልቅ ፡ ነህ ከአእምሮአችን ፡ በላይ ፡ ጥልቅ ፡ ነው ፡ ችሎታህ ሥራዎችን ፡ ሁሉ ፡ ስለ ፡ አንተ ፡ አወሩ ይሁን ፡ ስትላቸው ፡ ሆኑ ፡ ፍጥረታት ፡ በሙሉ ክብር ፡ ለሥምህ ፡ ይሁን (፪x)

