የሰው እጅ የሌለበት
Yesew Ej Yelielebet
ዳንኤል አምደሚካኤል · የሰው እጅ የሌለበት · 2013
አዝ፦ አዳነኝ ፡ በፀጋው ፡ አመሰግናለሁ ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ የሕይወቴ ፡ ጌታ ፡ ነው አምላክ ፡ በምህረቱ ፡ ባዘጋጀው ፡ መንገድ በወንጌሉ ፡ እምነት ፡ ሰጠኝ ፡ ዳግም ፡ ልደት በደስታ ፡ ከመዘመር ፡ ከማመስገን ፡ በቀር እኔማ ፡ ምን ፡ ልከፍል ፡ ከቶ ፡ ምን ፡ ልናገር የሰው ፡ እጅ ፡ የሌለበት ፡ የእኔ ፡ ብሎ ፡ የሚያኮራ በማመን ፡ የሚገኝ ፡ ጽድቅ ፡ የመስቀሉን ፡ ስራ ፀጋው ፡ በእምነት ፡ ሆኖ ፡ አድኖኛል እግዚአብሔር ፡ በልጁ ፡ ሕይወትን ፡ ሰጥቶኛል ሁሉ ፡ ተፈጸመ ፡ በመስቀሉ በሰላም ፡ እንድኖር ፡ በዘለዓለም፡ ፍቅሩ ላመስግነው ፡ በዝማሬ ፡ ይኼን ፡ ታላቅ ፡ ጌታ ከጨለማ ፡ ለነጠቀኝ ፡ ከዚያ ፡ ክፉ ፡ ቦታ ለወደደኝ ፡ ብርሃኑን ፡ ላበራ ፡ በሕይወቴ መልካም ፡ ዜማ ፡ ለእርሱ ፡ ይሁን ፡ ይክበር ፡ መድሃኒቴ አምላክ ፡ አበጃጀው ፡ ዘለዓለሜን አንድ ፡ ልጁን ፡ ሰጥቶ ፡ ክርስቶስ ፡ ብቃቴን የዘለላእም ፡ ህብረት ፡ ከአብ ፡ ጋራ አገኘሁ ፡ ልጅነት ፡ በክርስቶስ ፡ ስራ ምሥጋናውን ፡ ልዘምረው ፡ ልናገር ፡ ወንጌሉን ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ እንደሚያድን ፡ ላብስር ፡ ምስራቹን የአምላክ ፡ ፍቃድ ፡ ኢኼ ፡ ሆኗል ፡ ሰዎን ፡ የሚያመልጡበት በልጁ ፡ ደም ፡ በእግዚአብሔር ፡ ጽድቅ ፡ አምነው ፡ ሚድኑበት አዝ፦ አዳነኝ ፡ በፀጋው ፡ አመሰግናለሁ ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ የሕይወቴ ፡ ጌታ ፡ ነው አምላክ ፡ በምህረቱ ፡ ባዘጋጀው ፡ መንገድ በወንጌሉ ፡ እምነት ፡ ሰጠኝ ፡ ዳግም ፡ ልደት በደስታ ፡ ከመዘመር ፡ ከማመስገን ፡ በቀር እኔማ ፡ ምን ፡ ልከፍል ፡ ከቶ ፡ ምን ፡ ልናገር የሰው ፡ እጅ ፡ የሌለበት ፡ የእኔ ፡ ብሎ ፡ የሚያኮራ በማመን ፡ የሚገኝ ፡ ጽድቅ ፡ የመስቀሉን ፡ ስራ ምሥጋና ፡ ለአምላክ ፡ ፍቅር ፡ ለታደገኝ እግዚአብሔር ፡ ከጨለማ ፡ መንገድ ፡ መለሰልኝ ብርሃንን ፡ አሳየኝ ፡ ቅዱስ ፡ ቃሉ ተፈጸመ ፡ እንዳለ ፡ ጌታ ፡ በመስቀሉ ባመሰግን ፡ ይበዛል ፡ ወይ ፡ እኔስ ፡ በየእለቱ ቅኔን ፡ ብቀኝ ፡ ባሸበሸብ ፡ ብዘምር ፡ በቤቱ እልልስ ፡ ብል ፡ በታላቅ ፡ ድምጽ ፡ ብጮህ ፡ እስከደስታ ባጨበጭብ ፡ በመስቀሉ ፡ ለዚህ ፡ ክቡር ፡ ጌታ አዝ፦ አዳነኝ ፡ በፀጋው ፡ አመሰግናለሁ ኢየሱስ ፡ ክስቶስ ፡ የሕይወቴ ፡ ጌታ ፡ ነው አምላክ ፡ በምህረቱ ፡ ባዘጋጀው ፡ መንገድ በወንጌሉ ፡ እምነት ፡ ሰጠኝ ፡ ዳግም ፡ ልደት በደስታ ፡ ከመዘመር ፡ ከማመስገን ፡ በቀር እኔማ ፡ ምን ፡ ልከፍል ፡ ከቶ ፡ ምን ፡ ልናገር የሰው ፡ እጅ ፡ የሌለበት ፡ የእኔ ፡ ብሎ ፡ የሚያኮራ በማመን ፡ የሚገኝ ፡ ጽድቅ ፡ የመስቀሉን ፡ ስራ አሃ (፬x)

