Gubae

ሰማያዊ ፍቅር

Semayawi Fiker

ዳንኤል አምደሚካኤል · ልዘምር · 2019

ህይወት እንዳገኘ ባምላክ ምህረት እንዳረፈ ሰው በክፎቹ ጥላ ተሸሽጌ እዘምራለሁ በአይነቱ የተለየ ሰማያዊ ፍቅር ይዞኛል ግራ ቀኝ እንዳልል የኔ ወዳጅ ቤቱ ተክሎኛል አይደል አጋጣሚ ይሄስ የአምላክ ፍቅር ነው እንደኔ አይነቱን ሰው አጥቦ ልጅ ያደረገው እዎ ነፍሴ ረክታለች በዘላለም ጌታ ጨለማዬን ገፎ እስራቴን በፈታ እንዲህ ነው አይባል ቃላት አይገልፀው እየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ለኔ ያደርገው እራርቶልኝ የህይወቴን ታሪክ ለውጧል ባስደናቂው ፀጋ የእርሱ አድርጎኛል X2 ህይወት እንዳገኘ ባምላክ ምህረት እንዳረፈ ሰው በክፎቹ ጥላ ተሸሽጌ እዘምራለሁ በአይነቱ የተለየ ሰማያዊ ፍቅር ይዞኛል ግራ ቀኝ እንዳልል የኔ ወዳጅ ቤቱ ተክሎኛል ተመስግን እላለሁ ይክበር የሱስ ወዳጄ ፍቅሩ ልቤን ገዝቶት ሰላም ፈሶ በደጄ እውነት ነው ማዳኑ ሰንሰለት ይበጥሳል ይኸው ምስክር ነኝ ምህረቱ በኔ ታይቷል አገር ምድሩ ይስማ እየሱስ ያድናል ካፈር ላይ አንስቶ ያዘምረኛል እራርቶልኝ የህይወቴን ታሪክ ለውጥዋል ባስደናቂው ፀጋ የሱ አድርጎኛል X2 ህይወት እንዳገኘ ባምላክ ምህረት እንዳረፈ ሰው በክፎቹ ጥላ ተሸሽጌ እዘምራለሁ በአይነቱ የተለየ ሰማያዊ ፍቅር ይዞኛል ግራ ቀኝ እንዳልል የኔ ወዳጅ ቤቱ ተክሎኛል

ዳንኤል አምደሚካኤል · ሁሉም ዘማሪዎች