Gubae

ሰላም ይሰማኛል

Selam Yesemagnal

ዳንኤል አምደሚካኤል · ልዘምር · 2019

አዝ ፡ - ሰላሙን ጨምሮ ዘልቆ በህይወቴ ምንጩን አፈለቀ የእግዚአብሔር ፍቅር በመንፈስ ቅዱስ በውስጤ ፈሰሰ አስደናቂው ፀጋ ጉልበቴ ሆነኝ ሰላም ይሰማኛል ባርኮቱ ደርሶኛል እግዚአብሔር ለኔ ነው ይጠበቅኛል/ህይወት ሆኖኛል(2) አምላክ ያዘጋጀው የሱስ ያለም ቤዛ ያለም መድሃኒት እንዳልነዋወጥ ወጀቡ እንዳይጥለኝ ሆኖኝ መሰረት መንፈሱ ሞልቶኛል በቤቱ ተክሎኛል ዓለም የማይሰጠውን ሰላም ሰጥቶኛል (2) አዝ ፡ - ሰላሙን ጨምሮ ዘልቆ በህይወቴ ምንጩን አፈለቀ የእግዚአብሔር ፍቅር በመንፈስ ቅዱስ በውስጤ ፈሰሰ አስደናቂው ፀጋ ጉልበቴ ሆነኝ ሰላም ይሰማኛል ባርኮቱ ደርሶኛል እግዚአብሔር ለኔ ነው ይጠበቅኛል/ህይወት ሆኖኛል(2) የላቀ ደስታ ዓለምን የሚያስንቅ ሰላም ከሰማይ በቃሉ ላመኑ ከጌታ ተሰጥቷል ከሱ ዘንድ ከላይ ለኔም ይህን ደስታ ሰላም አግኝቻለሁ እየተደነቅኩኝ አመልከዋለሁ (2) አዝ ፡ - ሰላሙን ጨምሮ ዘልቆ በህይወቴ ምንጩን አፈለቀ የእግዚአብሔር ፍቅር በመንፈስ ቅዱስ በውስጤ ፈሰሰ አስደናቂው ፀጋ ጉልበቴ ሆነኝ ሰላም ይሰማኛል ባርኮቱ ደርሶኛል እግዚአብሔር ለኔ ነው ይጠበቅኛል/ህይወት ሆኖኛል(2) እግዚአብሔር በቃሉ በመንፈሱ ሙላት የባረካችሁ በደስታ እናምልከው እልልታው ይሰማ ይውጣ ድምፃችሁ ጌታችን ይመስገን ይደርደር በገና የሰላሙ ንጉስ እሱ/ኢየሱስ/ጌታ ነውና

ዳንኤል አምደሚካኤል · ሁሉም ዘማሪዎች