Gubae

ክቡር ስሙን

Kibur Simun

ዳንኤል አምደሚካኤል · እልልታ · 2024

ምህረቱ ፍቅሩ በዝቶልኝ ነው ኦ በደስታ ፊቱ ምዘምረው/2 ጌታ እየሱስ እጄን ይዞኛል መኖሪያዬን እርሱ ነው የመንፈሱን ደስታ ሰቶኛል ፊቱ ልቅረብ ላምልከው ኦ ዘውትር ክቡር ስሙን ልጥራው/2 ስሙ ድንቅ ነው ጌታ ዘላለም የከበረ በሰማይም በምድር እጅጉን የደመቀ አዕላፍ ይጠሩታል በፍቅሩ ያዳናቸው ጌታ እየሱስ የሚለው ስም መድሃኒት የሆናቸው ኦ ስሙ ይክበር ከስሞች ሁሉ በላይ ነው ከሱ ሌላ ደህንነትን መሻት ዘበት ነው በደስታ ደጋግሜ የጌታዬን ስም ልጥራው በደስታ ደጋግሜ የእየሱስን ስም ልጥራው ምህረቱ ፍቅሩ በዝቶልኝ ነው ኦ በደስታ ፊቱ ምዘምረው/2 ጌታ እየሱስ እጄን ይዞኛል መኖሪያዬን እርሱ ነው የመንፈሱን ደስታ ሰቶኛል ፊቱ ልቅረብ ላምልከው ኦ ዘውትር ክቡር ስሙን ልጥራው/2 እግዚአብሔር አብ እጅጉን ከፍ ከፍ አደረገው ከስምም ሁሉ በላይ የሆነውን ስም ሰጠው ጉልበት ሁሉ ለጌታ ለእርሱ ይንበረከካል ምላስ ለልዑል ክብር ጌታ ነው እየሱስ ይላል ኦ ሃሌሉያ ስግደት ይገባዋል ለንጉሱ የተበዣቸው ምስጋናን ዘመሩ በመቅደሱ በማደሪያው በህዝቡ መሃል ጌታን እያወደሱ/4

ዳንኤል አምደሚካኤል · ሁሉም ዘማሪዎች