በደስታ
Bedesta
ዳንኤል አምደሚካኤል · ልዘምር · 2019
በደስታ ላመልከው እጄን አነሳለው የከበረ ስሙን አመሰግናለው አመሰግናለው ቅዱስ ነው እግዚአብሔር ሁሉን የሚገዛ የነገስታት ንጉስ የጌቶቹ ጌታ የጌቶቹ ጌታ ቅዱስ ነው ማስተዋሉ የማይመረመር ቅዱስ ነው በሰማያት በክብር የሚኖር ቅዱስ ነው ለዘመኑ ፍፃሜ የሌለው ቅዱስ ነው ብርሃንን የተጎናፀፈው በደስታ ላመልከው እጄን አነሳለው የከበረ ስሙን አመሰግናለው አመሰግናለው ቅዱስ ነው እግዚአብሔር ሁሉን የሚገዛ የነገስታት ንጉስ የጌቶቹ ጌታ የጌቶቹ ጌታ ፃድቅ ነው የእውነት ዳኛ በፍርዱ ትክክል ፃድቅ ነው ፍፁም ገዢ ፍትህ ማያጓድል ፃድቅ ነው ትቢተኛውን እርሱ ያዋርዳል ፃድቅ ነው ለትሁታን ፀጋን ይጨምራል በደስታ ላመልከው እጄን አነሳለው የከበረ ስሙን አመሰግናለው አመሰግናለው ቅዱስ ነው እግዚአብሔር ሁሉን የሚገዛ የነገስታት ንጉስ የጌቶቹ ጌታ የጌቶቹ ጌታ ህያው ነው ለዘላለም የማይለውጠው ህያው ነው ትላንት ዛሬም ሁሌም ያው የሆነው ህያው ነው መጀመሪያም መጨረሻም የለው ህያው ነው ልዑል አምላክ ፍጥረት የሚያመልከው በደስታ ላመልከው እጄን አነሳለው የከበረ ስሙን አመሰግናለው አመሰግናለው ቅዱስ ነው እግዚአብሔር ሁሉን የሚገዛ የነገስታት ንጉስ የጌቶቹ ጌታ የጌቶቹ ጌታ

