ጌታን ነው የያዝኩት
Gietan New Yeyazkut
ዳግማዊ ጥላሁን · ቃልህ ቃሌና ግብሬ · 2010
አንተ ፡ ባትደረስ ፡ ባታየኝ ፡ ኖሮ አይዞህ ፡ ያለኝ ፡ ሰው ፡ ድንገት ፡ ተሰብሮ ባበቃ ፡ ነበር ፡ እዛ ፡ ላይ ፡ እኔስ ፡ ታሪኬ አዋጅ ፡ ባይሻር ፡ የሞቴ ፡ ባንተ ፡ ባምላኬ (፪x) ሰው ፡ አለኝ ፡ አይደለም ፡ ያልኩት ጌታን ፡ ነው ፡ እኔስ ፡ የያዝኩት (፬x) መመኪያዬ ፡ መታመኛ ፡ ነው እሱን ፡ ይዤ ፡ ታዲያ ፡ እንዴት ፡ ፈራለሁ (፪x) ሰው ፡ አለኝ ፡ አይደለም ፡ ያልኩት ጌታን ፡ ነው ፡ እኔስ ፡ የያዝኩት (፪x) በስብርባሪውም ፡ እደርሳለሁ ፡ እንጂ አልቀርም ፡ ስምጬ ፡ ይዤ ፡ የአንተን ፡ እጅ ይዤ ፡ ጌታን ፡ ይዤ ይዤ ፡ ጌታን ፡ ይዤ ፡ ሆ ይሞታል ፡ እያሉ ፡ ይጠባበቃሉ እሱን ፡ ይዞ ፡ ያፈረ ፡ ማንን ፡ ሰው ፡ ያውቃሉ ይዤ ፡ ጌታን ፡ ይዤ ይዤ ፡ ጌታን ፡ ይዤ ፡ ሆ መመኪያዬ ፡ መታመኛ ፡ ነው እሱን ፡ ይዤ ፡ ታዲያ ፡ እንዴት ፡ ፈራለሁ (፪x) በእርግጥ ፡ ወጀብ ፡ ካለ ፡ ታንኳ ፡ አይለቀቅም ና ፡ ካለኝ ፡ ግን ፡ ጌታ ፡ ልቀር ፡ አላስብም ይዤ ፡ ጌታን ፡ ይዤ ይዤ ፡ ጌታን ፡ ይዤ ፡ ሆ በድካም ፡ በብርታት ፡ አሳልፎ ፡ የማይሰጥ እሱን ፡ መያዝ ፡ እንጂ ፡ ማዕበሉን ፡ ለማምለጥ ይዤ ፡ ጌታን ፡ ይዤ ይዤ ፡ ጌታን ፡ ይዤ ፡ ሆ ሰው ፡ አለኝ ፡ አይደለም ፡ ያልኩት ጌታን ፡ ነው ፡ እኔስ ፡ የያዝኩት (፬x) ለዚህች ፡ አጭር ፡ ዘመን ፡ ለዚህች ፡ አጭር ፡ ጊዜ ቅርት ፡ ይበል ፡ ሁሉም ፡ ዘላለሜን ፡ ይዤ ይዤ ፡ ጌታን ፡ ይዤ ይዤ ፡ ጌታን ፡ ይዤ ፡ ሆ አንዱም ፡ አላረካኝ ፡ አንዱም ፡ ውስጤ ፡ አልገባ አንተን ፡ ስይዝህ ፡ ነው ፡ የደረቀው ፡ የኔ ፡ እንባ ይዤ ፡ ጌታን ፡ ይዤ ይዤ ፡ ጌታን ፡ ይዤ ፡ ሆ መመኪያዬ ፡ መታመኛ ፡ ነው እሱን ፡ ይዤ ፡ ታዲያ ፡ እንዴት ፡ ፈራለሁ (፪x)

