የሰላም መፍለቂያ
Yeselam Mefleqiya
ካሌብ ተስፋዬ · ትንሳኤ አለ · 2009
ዘማሪ ካሌብ ተስፋዬ ርዕስ የሰላም መፍለቂያ አልበም ትንሳኤ አለ የሰላም መፍለቂያ ምንጭ ነህ ኢየሱሰ አንተ እውነተኛ ዓለም ለቀጣው ሰው ለተጐዳ መጽናኛ የጠፋን ፈላጊ የኃጢአተኛ ወዳጅ ለበዛው በደሉ ጠበቃ ነህ አማላጅ ስንቱ እረፍት አጥቶ ኖረ መስሎት ብዙ ሞከረ ለፋ ወጣ ገባ ፈልጐ አላገኘም ምህረትህ ቀደመ ከንቱ ሆኖ አልቀረም የሰላም መፍለቂያ ምንጭ ነህ ኢየሱሰ አንተ እውነተኛ ዓለም ለቀጣው ሰው ለተጐዳ መጽናኛ የጠፋን ፈላጊ የኃጢአተኛ ወዳጅ ለበዛው በደሉ ጠበቃ ነህ አማላጅ እምቢ አሻፈረኝ ብሎ ሄደ ቤትህን ጥሎ በፍቅር አባብለህ መለስከው ያንን ሰው አንተን መሳይ አባት ከየት ነው እሚገኘው የሰላም መፍለቂያ ምንጭ ነህ ኢየሱሰ አንተ እውነተኛ ዓለም ለቀጣው ሰው ለተጐዳ መጽናኛ የጠፋን ፈላጊ የኃጢአተኛ ወዳጅ ለበዛው በደሉ ጠበቃ ነህ አማላጅ ነፍሱን ለጠሉት ሁሉ ሲል ሰጠ ተቆጠረ እንደ ቂል የሰው ልጆች ክፋት እንዲህ እየጨመረ ምትክ ሆኖ ባይሞት ምን ይኮን ነበረ? የሰላም መፍለቂያ ምንጭ ነህ ኢየሱሰ አንተ እውነተኛ ዓለም ለቀጣው ሰው ለተጐዳ መጽናኛ የጠፋን ፈላጊ የኃጢአተኛ ወዳጅ ለበዛው በደሉ ጠበቃ ነህ አማላጅ።

