ይታይ
Yita
ቢንያም ዋለ · ያየ ይናገር · 2017
የማይሰወር እንግዳ ነገር አድርግና ይታይ ክብርህ በእኔ ላይ ይታይ እጅህ በእኔ ላይ ይታይ ምሕረትህ በእኔ ላይ ይታይ ብርሃንህ በእኔ ላይ የጥበብ እና የመገለጥ መንፈስ ጌታ ሆይ በሙላት በልቤ ላይ ይፍሰስ ለአይሁድ ለግሪክ ሰው ለጨዋ ለባሪያ እንድሆን አድርገኝ ወንጌልን ማብሰሪያ በምልክቶች በድንቅ ነገር በልዩ ልዩ የአንተ ተአምር በመንፈስ ቅዱስ ምስክርነት ጌታ ሆይ ክብርህ ይታይ በእኔ ሕይወት ከልቤ መሻት ከቃሌም በላይ ማዳንህ ደምቆ ክብርህም ይታይ ይታይ ክብርህ በእኔ ላይ ይታይ እጅህ በእኔ ላይ ይታይ ምሕረትህ በእኔ ላይ ይታይ ብርሃንህ በእኔ ላይ የሕይወቴ ብርሃን በሁሉ ፊት ይብራ እንዳለህ ይታወቅ አንተ ከእኔ ጋራ ይሁን መላ ሕይወቴ በክብርህ ሙሉ አትደበቅ ከቶ ይይህ ያየኝ ሁሉ በምልክቶች በድንቅ ነገር በልዩ ልዩ የአንተ ተአምር በመንፈስ ቅዱስ ምስክርነት ጌታ ሆይ ክብርህ ይታይ በእኔ ሕይወት ከልቤ መሻት ከቃሌም በላይ ማዳንህ ደምቆ ክብርህም ይታይ ይታይ ክብርህ በእኔ ላይ ይታይ እጅህ በእኔ ላይ ይታይ ምሕረትህ በእኔ ላይ ይታይ ብርሃንህ በእኔ ላይ እስካይቻል ድረስ ፍጹም ለመሸሸግ በሐዋርያቱ እጅ ተአምርን ስታደርግ እንደተደነቀ ሕዝቡ ክብርን አይቶ በእኔም ክብርህ ይታይ አይሸሸግ ከቶ በእኔም ክብርህ ይታይ አይሰወርም ከቶ በእኔም ክብርህ ይታይ አይደበቅ ከቶ በእኔም ክብርህ ይታይ አይሸሸግ ከቶ በእኔም ክብርህ ይታይ አይሰወር ከቶ

