ተይዛለሁ
Teydzalehu
ቢንያም ዋለ · ያየ ይናገር · 2017
በቅኔ ላጫውትህ እውነቱን እናውጋ የመወደዴን ልክ የፍቅርህን ዋጋ የትኛውም ሆሄ ቋንቋና ሰዋሰው አይችልም በጭራሽ ፍቅርህን ሊገልጸው ሸፍኖታል ፍቅርህ የበደሌን ብዛት የዘመኔን እርቃን የነፍሴን እርዛት ኃጢአቴ ተሽሯል የለብኝም ሐፍረት ወደ አንተ ለመቅረብ አግኝቻለሁ ድፍረት አመሰግናለሁ አመሰግናለሁ በፍቅርህ ስለያዝከኝ አመሰግናለሁ የፍቅርህ አሻራ በልቤ ታትሞ ስለ ነገ ልቤ አይሰጋም ፈጽሞ ከቶ አይናወጥም በከበበው ማዕበል ተማምኖብህ ያድራል በስጋት መካከል የአንተ አድርጎኛል ፍቅርህ አሸንፎ እድፋሙን ጥምጣም ከላዬ ላይ ገፎ ሙላት ሆኖልኛል አያሻኝም ሌላ በፍቅርህ ኖራለሁ ከአንተ ጋር በተድላ ማዕበሉ ቢያይል ሕይወቴን ሊያሰጥም ፍቅርህ መልሕቄ ነው ከቶ አልናወጥም ምንም አይነካኝም የአንተን ፍቅር አልፎ እንዳልሰናከል ይዞኛል ደግፎ ተይዣለሁ በፍቅርህ እኔ አልሰጋም(4*)

