ታርደሃልና
Tardehalina
ቢንያም ዋለ · ያየ ይናገር · 2017
ብርቱ መልአክ እንዲህ ሲል አወጀ ማኅተሙን ለመፍታት ማነው የተዘጋጀ በሰማይም በምድርም አልተገኘም ከቶ መጽሐፉን ለመውሰድ ለመመልከት ከፍቶ ግን አንተ ተገኘህ የታረድከው በግ ለአንተ ተችሎሃል ይህንን ማድረግ መጽሐፉን ወሰድከው ማኅተሙ ተፈታ ሁሉን ድል ነሥተሃል ኢየሱስ ነህ ጌታ ታርደሃልና ይገባሃል ክብር*4 ቀራንዮ ላይ እርቃንህን ተንጠልጥለህ አሸንፈሃል በመስቀልህ ጥልን ገድለህ በትንሳዔ ኃይል የሞትን ጣር አጥፍተህ ድል ነሥተሃል ሰባቱንም ማኅተም ፈተህ ከነገድ ከቋንቋ ሕዝብህን ዋጅተሃል ካህንና መንግሥት ሕዝብን አድርገሃል ክብር ይገባሃል*8

