ስሙን ቀደሰ
Simun Kedese
ቢንያም ዋለ · ያየ ይናገር · 2017
የማይሆን ነገር ሆነልኝ የማይቻለውን አስቻለኝ እግዚአብሔር በሕይወቴ ስሙን ቀደሰ የነገሥታትን ትጥቅ ወገብ ሊፈታ በሮቹን ሊከፍት ሰባሪው ጌታ ቀኝ እጄን ይዞ እንደ ቂሮስ ከፊቴ ቀድሞ ሆነኝ ሞገስ ሰብሮት ከፊቴ የናሱን በር ማለፍ ሆኖልኛል በድል መሻገር ተራራውን ናደ አረገው ሜዳ ድንቅ አደረጎ እኔን ረዳ ክብር ለስምህ ይሁን ክብር*4 ጌታ አፈራርሶ የሐማን ሴራ ሕዝቡን ለማዳን ተዓምርን ሠራ በእኔም ሕይወት ጌታ ተገልጦ ስሙን ቀድሷል ነገር ገልብጦ የማይቻል ነገር ለሰው የተሳነ ኃይልን በሚሰጠኝ በሱ ለኔ ሆነ ከኔ ጋር መሆኑ እሱ ነው ስኬቴ በረከት ሆነልኝ ገብቶ ወደ ቤቴ ክብር ለስምህ ይሁን ክብር*4 ማይመረመር የማይቆጠር ያደርጋል ጌታ ድንቅ ታምር ባለቀ ሰዓት ከተፍ ይልና በሳቅ ይሞላል በድል ምስጋና ክብር ለስምህ ይሁን ክብር*4

