ምርጫዬ ልክ ነው
Mirchaye Lik New
ቢንያም ዋለ · ያየ ይናገር · 2017
አጣሁኝ ብዬ ከቶ አይቆጨኝም ከዓለም የሆነውን ፈጽሞ አልመኝም የቀረብኝ ሁሉ እንኳን ቀረ ያኔ በጌታ በኢየሱስ ተውቧል ዘመኔ ምን ቀረብኝ ምን ጎደለብኝ የዚህን ዓለም ነገር ስለተውኩኝ የቀረብኝ ሞት ነው የዘላለም ቁጣ ወትሮስ ምን ሊኖረው ኢየሱስን ያጣ አተረፈ እንጂ በነፍስም በሥጋው ኢየሱስ ክርስቶስ የሆነለት ዋጋው ከንቱ ነው የምድር ንዋይ የከበረውን አሻቅቦ ለሚያይ ምርጫዬ ልክ ነው በእርግጥ ያዋጣል ከዓለም ሀብት ክብር ኢየሱስ ይበልጣል እውነቱ ለገባው ለበራለት ሐቁ የተወደድክ ነህ የምትልቅ ከዕንቁ የሙጥኝ ልበልህ እኔም በአንተ ልጽና ከምንም የምትበልጥ በረከት ነህና እንደሚርቅ እንዲሁ ሰማይ ከምድር ኢየሱስን ማወቅ ነው ታላቅ ምስጢር ብርሃን ከጨለማ አንድ እንዳልሆነ ልዩ ነው አድራሻው በኢየሱስ ያመነ ከንቱ ነው የምድር ንዋይ የከበረውን አሻቅቦ ለሚያይ ምርጫዬ ልክ ነው በእርግጥ ያዋጣል ከዓለም ሀብት ክብር ኢየሱስ ይበልጣል ሞት አለፈኝ ውርደት አለፈኝ ችግር አለፈኝ ጌታ ስላለኝ

