ከፀሐዩ በላይ
Ketsehayu Belay
ቢንያም ዋለ · ያየ ይናገር · 2017
ከፀሐዩ በታች በሚታየው ዓለም ሁሉ እንደወትሮው ነው አዲስ ነገር የለም ድግግም ነው አዙሪቱ ዞሮ ይመጣል የትናንቱ ከፀሐዩ በላይ አለ አዲስ ነገር ያለና የነበረው የሚኖረው ትልቁ እግዚአብሔር አሁንም ቅድምም ዛሬም ትናንትና በማያረጅ ክብር በማይከስም ዝና ደምቆ ይኖራል ጌታ ለዘለዓለም በሰማይ በምድር የሚመስለው የለም ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ የሠራዊት አምላክ በሰማይ የሚኖር ከፍ ያለ ያለ ልክ ከፀሐይ ሰባት እጅ የሚያበራ ደምቆ ገናና ነው እርሱ አይጨረስ ታውቆ በሰማይ ከፍ ያለ ኃያል አምላክ አለ የማይቀየር ለአፍታ ከቶ ለዘላለም ሚኖር ጸንቶ

